በመቀሌ ከተማ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ።በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ ከተማ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን በክልሉ ያሉ አሸከርካሪ እና ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/E16WNc26_ubDrxuZI6SzCusPXR01nGpJhzpnjs4rkrO8rE-crDP_mx87oVvTmX9vFkFmoq4plE1jp-unhP5UJQf1BEq2t09v3ndGeti_h7rPeFFRkP86NYNIpHPquvFfLHjNN4JYeoZbng6CkSZX39XjsW8PzHnUrbf6eCmHHSWB2ApADq3kUYoXdvpwosMJWFkxj7pmc_6v9u28aPE28jUib548suAMMGu2ACqCCuRePhSZDnb947fLcpDx2gwWBJh6hdHVc3OwiRYHdFlll_lCuKFfkzv9wvcDj1j_pjudp8FnMhOCUsgAVgKwjyLlPchhPckUbgTiw5nVeJyXAg.jpg

በመቀሌ ከተማ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ።

በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ ከተማ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን በክልሉ ያሉ አሸከርካሪ እና ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በከተማዋ ባለፋት ሶስት እና አራት ቀናት ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ገልፀዋል።

በከተማዋ አንድ ቦታ ብቻ ቤንዚን መኖሩን ነው የገለጹት።
በዚህም ቤንዚን እስከ 120 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ የሚያነሱት አሽከርካሪዎቹ፣ ናፍጣ ግን አሁንም ድረስ እንደሌለ አስረድተዋል።

በዚህም በትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ ሙሉ በሙሉ ጭማሪ ለማድረግ እንደተገደዱ ተናግረዋል።

የነዳጅ የጠፋበትን ምክንያት በውል ባያቁትም ማታ ማታ በጄሪካን በብዛት ከማደያ እየተቀዳ እንደሚሄድ እንደሚያዩና የት እንደሚሄድ ግን እንደማያቁ ገልፀዋል።
በከተማዋ የነደጅ እጥረት ሲከሰት ይህ የመጀመሪያ እንዳልሆነ ሲገለፅ ከዚህ ቀደም በስፋት ማጋጠሙ ይታወሳል።

በለአለም አሰፋ

ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply