በመቀሌ ከ2 መቶ ሺ በላይ የሚገመቱ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አንደሚያስፈልጋቸው ተጠቆመ፡፡

ጦርነቱ ባስከተለው ጉዳት በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፋ እንደሚያስፈልጋቸው ነው የተገለጸው፡፡የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለአሐዱ እንተናገሩት በአጠቃላይ 80ሺ የሚገመቱ እርዳታ ፈላጊዎች እንዳሉ ቀደም ብሎ የተገመተ ሲሆን አሁን ላይ በመቀሌ ብቻ ከ2 መቶ ሺ በላይ የሚገመቱ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ የሚሹ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ምንያህል ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል የሚለውን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ ጥናት እየተደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡በሚደረገው የጥናት ውጤትም እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ቁጥራቸውን ከማወቅ ባለፈ ምን ያህል ድጋፎች ያስፈልጋሉ የሚለውንም ለማወቅ ያስችላል ብለዋል፡፡

የተለያዩ ድጋፎች ለማድረግ ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ አታክልቲ በክልል ደረጃ በእርሻ ልማት ስር መረጃን በማደረጃት እርዳታ ማድረግ ለሚፈልጉ ረጂ ድርጅቶች የሚያደርስ የስራ ዘርፍ መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡በጥናቱ ውጤትም ምን ያህል ዜጎች እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ማን ምን አይነት ድጋፍ አደረገ የሚለውን ለህዝቡ ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡

*************************************************************************

ዝጋቢ፡ፍቅርተ ቢተው

ቀን 21/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply