በመተሀራ አልጌ ቀበሌ የተፈጠረው ምንድነው?በትላንትናው እለት በመተሀራ ከተማ አስተዳደር ፈንታሌ ወረዳ አልጌ ቀበሌ በመዝናኛ ቦታ ላይ የነበሩ ወጣቶች ማንነታቸው ባልተወቀ ታጣቂዎች ጥቃት ደር…

በመተሀራ አልጌ ቀበሌ የተፈጠረው ምንድነው?

በትላንትናው እለት በመተሀራ ከተማ አስተዳደር ፈንታሌ ወረዳ አልጌ ቀበሌ በመዝናኛ ቦታ ላይ የነበሩ ወጣቶች ማንነታቸው ባልተወቀ ታጣቂዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከመተሀራ በትላንትናው እለት በነበረው ጥቃት 10 የሚጠጉ ወጣቶች ፑል እየተጫወቱ ሳለ በታጣቂዎች ተገለዋል የሚል መረጃ ደርሶት ነበር፡፡

ይህ ብቻ አይደለም ከ11 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች መቁሰላቸውን ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የመተሀራ ከተማ ነዋሪዎች ነግረውን ነበር፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ጉዳዩን በተመለከተ የመተሀራ ከተማ አስተዳደር የፈንታሌ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ፍሬዘር አበራን አነጋግረናል፡፡

እርሳቸው በተባለው ቀበሌ እስካሁን ማን እንደሆኑ በውል ያልታወቁ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው የአምስት ወጣቶች ህይወታቸው እንደቀጠፉ ፣ እንደሁም ሌሎች አምስት ወጣቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው መተሀራ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በመተሃራ ፈንታሌ ወረዳ አልጌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከዚህ በፊትም እንደዚሁ ተመሳሳይ ጥቃት ተከስቶ እንደነበረ ዋና አስተዳዳሪው አስታሰዋል፡፡

አሁን የተከሰተው ጥቃት ከብሄር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው አቶ ፍሬዘር ለጣቢያችን አረጋግጠዋል፡፡

ጥቃት የተፈጸመበት አካባቢ የኦሮምያ ፖሊስ እና የክልሉ ልዩ ሀይል በጥቃቱ የተሳተፉትን አካላት እያደኑ ይገኛሉ ሲሉ አቶ ፍሬዘር ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 09 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply