በመተማ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ

በመተማ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው በወረዳው ትናንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ30 ከሽመለጋራ ተነስቶ ወደ ኮኪት ቀበሌ ሰሊጥ ጭኖ በመጓዝ ላይ ያለ ማርቸዲስ የጭነት ተሽከርካሪ ከጭነቱ በላይ ሰባት ሰዎችን እንደጫነ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት በመገልበጡ የደረሰ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ረዳቱን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን ከመተማ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post በመተማ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply