በመተከልና በወለጋ የሚደረገው የዘር ማጥፋት ወንጀልን መቆም እንዳለበት ተገለጸ                   አሻራ ሚዲያ            ታህ…

በመተከልና በወለጋ የሚደረገው የዘር ማጥፋት ወንጀልን መቆም እንዳለበት ተገለጸ አሻራ ሚዲያ ታህ…

በመተከልና በወለጋ የሚደረገው የዘር ማጥፋት ወንጀልን መቆም እንዳለበት ተገለጸ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-7/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር እንደሚታወቀው ላለፉት አምስት ወራት በመተከልና በወለጋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ማቆሚያ ባላገኘ መፈናቀል፣ መገደልና መሳደድ ውስጥ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ እንዲሁም ባሳለፍነው የጥቅምት ወር ውስጥ በወለጋ የሚኖሩ ኢ-መደበኛ ሠራዊት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ አማራዊያንን ኑ ለስብሰባ እንፈልጋችኋለን በሚል ከሰበሰባቸው በኋላ በእጅ ቦምቦችና በመትረየስ ዘግናኝ ጭፍጨፋ የፈፀሙባቸው መሆኑም ይታወሳል፡፡ በዚያው ጥቅምት ወር ላይ በጉራፈርዳ ለፀሎት በመስጊድ በተገኙ ቁጥራቸው 38 የሚደርሱ አማራዊያንንም በጅምላ አርዶ መግደሉ የቅርብ ግዜ ትውስታ ነው። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በወቅቱ ተገቢውን የችግር ምንጭ ከመግለፅ ይልቅ ሁሉንም ጥፋቶች በሙሉ ለትህነግ በማሸከም የራሱን የመስፋፋት ዘመቻ ውጤት የጥፋት ድርጊት በትህነግ ሲያሳብብ ቆይቷል። ትህነግ ለአማራ ህዝብ መጥፋት ቀን ከሌሊት የሚተጋ ፋሽስታዊ የምንጊዜም ጠላት ቢሆንም በአማራ ላይ ለተከሰቱና ለሚከሰቱ ጥፋቶች ሁሉ ብቸኛው ተጠያቂና ምክንያት ትህነግ ነው ብለን አናምንም። ትህነግ በሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ፈፅሞ ወደ አማራ ርስት ያደረገው የወረራ ሙከራና ትንኮሳ መመከት ያለበትና በተገኘው አጋጣሚ ትህነግን መቅበር በሀይል የተነጠቁ ርስቶችንም በሄዱበት አግባብ መመለስ አስፈላጊ በመሆኑ የሰሜንና የምስራቅ አማራ ጥያቄዎቻችንንም መልሳቸውን በወንድሞቻችን ደም መመለሳችን የምንኮራበት እንጂ በምንም መልኩ የምንፀፀትበት አይደለም ። ነገር ግን ከጦርነቱ መጀመር አንስቶ በቀጣይ የሚኖረው የሀይል አሰላለፍ የአማራን ህዝብ ፅናትና ህዝባዊ አንድነት የሚጠይቅ መሆኑን መታወቅ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ለብዙ ጊዜያት በአማራ ህዝብ ላይ ያለአንዳች ዕረፍት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጥራት ወንጀል እያስፈፅመበት ያለው የቤኒሻንጉል ክልል መንግስት በአሁኑ ሰአት ጭፍጨፋውን ይበልጥ በማፋፋም በወለጋ ኦነግ ከተሰኘ ኢ-መደበኛ ሠራዊት ጋር በመናበብ ንጹሀን አማራዎችን እያስጨፈጨፈ ይገኛል። በቁስል ላይ ጥዝጣዜን ለመጨመር በሚመስል መልኩም ቤኒሻንጉልን የሚያስተዳድረው አሻድሊ ሐሰን ከኦነግ ሀይል ጋር በማበር የህዝባችንን ክብር ዝቅ የሚያደርግ ዘለፋና ስድብ በመግለጫ ስም እያሰራጨ ይገኛል። በመተከል እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥራትና የዘር ማጥፋት ወንጀል በኦሮሚያክልል በስልጣን ላይ በሚገኘው አመራር አቀነባባሪነት በቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግስት መዋቅር አስፈፃሚነት የሚደረግ የውክልና ጦርነት መሆኑን ምንጮች ገልጸውልናል። ስለሆነም በመተከልና በወለጋ አካባቢ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚመለከተው አካል ተከታትሎ አጥፊውን ለህግ ማቅረብ ለተበዳዩም ደግሞ ፍት ህ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም በመተከልና በኦሮሚያ ክልል ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በአካባቢው የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች በህግ ሊጠየቁ እንደሚገባ ምንጫችን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply