በመተከል:ኦሮሞ ክልል:በማይካድራና በግድምና ኢፍራታ ለተጨፈጨፉት ወግኖቼ መታሰቢያ ትሁንልኝ:: ===================================== ወገን ተጨፍጭፎ ማይካድራ ወደቀ:…

በመተከል:ኦሮሞ ክልል:በማይካድራና በግድምና ኢፍራታ ለተጨፈጨፉት ወግኖቼ መታሰቢያ ትሁንልኝ:: ===================================== ወገን ተጨፍጭፎ ማይካድራ ወደቀ: ልጅ አዋቂ አላለም:ወንድ ሴት አላለም:… ወጣት ሽማግሌ ሁሉም ሰው አለቀ: በዱር በገደሉ:በጫካ በደኑ አማራው ወደቀ: በአጥንት በደሙ :ባቀናት አገር ላይ አፈር ሳያለብሱት: ቀን ለአሞራምሣ: ማታ ለጅብ እራት የትም ወረወሩት:: ዋ ! እኔን አፈር ይብላኝ :አምራው ይጋጠኝ! ስትጮህ ያልደረስኩ! ቆሜ ያልቀበርኩህ! ከነርሜ የበላሁ:ውለታ ቢሱ ነኝ:: አለቀ አሉኝ ወገን:መተከል :ወለጋ; በጦር በጎራዴ :በቀስት:ተወጋ; በክላሽ: በብሬን:በመትረየስ ጥይት ተጨፍጭፎ አማራ: የትም ወድቆ ቀረ:የሚቀብረው ጠፍቶ ጅብ በላው አሞራ:: ሚስትና ልጆቹን: እሱንም ጨምረው: ቤቱን በላዩ ላይ ከውጪ ቆልፈው: እሣት ለቀቁበት :ለብልበው እጋይት: አጥንቱ እልተገኘም አመድ አደረጉት:: እርጉዝ ተገደለች: የምታጠባ እናት: ጉበት:ካላሊቷን እውጥትውም በሉት:: በአውቶቢስ ተጭነው: አማራ ፍለጋ: ታጥቀው ገስገሱ: አጣዬ: ጥሙጋ: የነአጅሬን አገር የነ አይደፈሬ: ኢፍራታና ግድም: አሽኳይና ከሬ: ለክፉ ቀን ደራሽ: በሰላም ገበሬ: ሄደው ጨፈጨፉት ገብተው ከመደሩ: ባዙቃ: መትርየስ:በክላሽ:በስናይፐር: ጥይት ሲይዘንቡቡት :ጀግናው:ሳይበገር: ቀጥ አርጎ አቆማቸው: ባልቤን በምንሽር:: እንኳን ቤልጅግ ይዞ! እንኳን ጏንዴ ይዞ! መትረየስ ይቀማል ጎራዴውን መዞ:: ወገብ ሙሉ ጥይት ዝናር የታቀፉ: አማራን ለማጥፋት ለጦር ቢሰለፉ: ደረታቸው ሰፍቶ: ምን ቢደነድኑ: መች ደነግጣል ይፋቴ ጅንኑ! ይጋፈጣል እንጂ መሸሽን የት ያውቃል! እየጣለ:መውደቅ:እየረፈረፈ በደንብ ያውቅበታል:: አይዞህ ወገኔ! አይዞህ! ወንድሜ! እደርስልሃለሁ እኔም ባለኝ አቅሜ:: ይፍሩ ኃይሉ ከስሜን አሜሪካ April 8,2021

Source: Link to the Post

Leave a Reply