በመተከል ለሚካሄደው ጭፍጨፋ መንግሥት  ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል ሲል ባልደራስ ገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል…

በመተከል ለሚካሄደው ጭፍጨፋ መንግሥት ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል ሲል ባልደራስ ገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል…

በመተከል ለሚካሄደው ጭፍጨፋ መንግሥት ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል ሲል ባልደራስ ገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል እየተፈፀመ ያለው መንግሥታዊ ጅምላ ጭፍጨፋ አሁንም እንደቀጠለ ነው ብሏል ባልደራስ ዛሬ ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ። ባልደራስ በመግለጫው በመተከል ተከታታይ የጅምላ ጭፍጨፋ ብቻ ሳይሆን የጅምላ ቀብር ጭምር እተፈፀመ ይገኛል፤ ይህም የዘር ማጥፋቱ የመጨረሻው ማረጋገጫ ተደርጎ ይወሰዳል ነው ያለው። ድርጊቱ የሚፈፀመው በመንግሥታዊ መዋቅሮች ታግዞ እንደሆነ የሚታመን ሀቅ ነው ያለው ባልደራስ አንዳንድ አመራሮችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ቢሞከርም ከዜና ፍጆታ የዘለለ ተግባር አልታየም ብሏል። ድርጅቱ ሲቀጥል ከስልጣን በተነሱት አመራሮች ምትክ ሌላ ጨፍጫፊ ይመደባል፤ አንዳንድ ጊዜ ራሳቸውም ተመልሰው በሌላ የጭፍጨፋ አሰላለፍ ይገኛሉ፤ በመሆኑም የዘር ማጥፋቱ ተባብሶ ቀጥሏል ነው ያለው። መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጭምር በሪፖርቱ እንዳመላከተው ነሐሴ 29፣ 30 እንዲሁም ጳጉሜ 1 እና 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በቀድሞው የጎጃም ክፍለ ሀገር፤ መተከል ጉባ፣ ድባጢ፣ ቡለን እና ወንበራ ወረዳዎች ውስጥ ንፁሀን አማራዎች በጅምላ ተገድለዋል። ሕዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም ከወንበራ ወደ ቻግኒ ሲሽከረከር የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ቂዶህ ቀበሌ ሲደርስ በታጣቂዎች በተፈፀመ ዘግናኝ ጥቃት ከ38 በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ተመሳሳይ ጥቃት መድረሱን የኢሰመኮ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፤ ይህም ኢትዮጵያውያን ዕለት በዕለት የምናየው ሀቅም ነው ብሏል። ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ ደግሞ በቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ከሌሊቱ አስር ሰዓት ጀምሮ በታጣቂዎች በተከፈተ ጥቃት ከመቶ በላይ ንፁሀን ተገድለዋል ያለው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በኢሰመጉ ሪፖርት መሰረት ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ከአምስት መቶ በላይ ንፁሀን ተገድለዋል፤ በተያያዘም ከመቶ ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ የሟቾችን ቁጥር ደግሞ የመገናኛ በዙሃን ዘገባዎች ከዚህም በላይ ከፍ ያደርጉታል ነው ያለው። ለተፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋ መንግሥታቸው ኃላፊነቱን ሊወስድና በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል ሲል ነው ባልደራስ ያሳሰበው። ይህንን ሁሉ ጭፍጨፋ መንግስት ባለማስቆሙ ዜጎች ተፈጥሮዓዊ መብታቸውን ተጠቅመው ራሳቸውን እንዲከላከሉ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ጠይቋል። አገርን ከማዳን አንፃር ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተባብረን እንስራ ሲል ነው ባልደራስ ጥሪውን ያቀረበው፡፡ የፊታችን ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ባልደራስ በሚያስተባብረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በመገኘት ጭፍጨፋውን እንድትቃወሙ በድጋሜ ጥሪ እናቀርባለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply