በመተከል ቀውስ እንዲረጋጋ ኦነግ ሸኔ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ አለበት – የቢሻንጉል ክልል ኮሚኒኬሽን፡፡ (አሻራ ጥር 3፣ 2013 ዓ.ም) የቢሻንጉል ጉምዝ ክልል ኮሚኒኬሽን ከህዝብ ስብሰባዎች ተ…

በመተከል ቀውስ እንዲረጋጋ ኦነግ ሸኔ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ አለበት – የቢሻንጉል ክልል ኮሚኒኬሽን፡፡ (አሻራ ጥር 3፣ 2013 ዓ.ም) የቢሻንጉል ጉምዝ ክልል ኮሚኒኬሽን ከህዝብ ስብሰባዎች ተ…

በመተከል ቀውስ እንዲረጋጋ ኦነግ ሸኔ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ አለበት – የቢሻንጉል ክልል ኮሚኒኬሽን፡፡ (አሻራ ጥር 3፣ 2013 ዓ.ም) የቢሻንጉል ጉምዝ ክልል ኮሚኒኬሽን ከህዝብ ስብሰባዎች ተረዳሁት ባለው ዘገባው መሰረት የኦነግ ሸኔ ሀይል እና በክልሉ ውስጥ ያሉ የህወኃት አመለካከት ተሸካሚዎች መጥፋት አለባቸው ብሏል፡፡ የእርስ በእርስ መጠራጠር እና መፈራረጅ እንዲኖር ህወኃት የጥላቻ ፖለቲካ መስርቷል፡፡ ጥላቻውን ደግሞ ኦነግ ሸኔ እና የጉምዝ ታጣቂዎች ወስደው ንፅሃንን እያፈናቀሉ ነው ብሏል፡፡ የመተከል ኮማንድ ፓስትም የነባር እና የመጤ ትርክቱ እንዲስተካከል የአመለካከት ስራ በስፋት ይጠይቃል ብሏል፡፡ ክልሉ አመራር አሰያየም ላይ በህዝብ የተመረጡ አመራሮች እንዲመሩ አደርጋለሁ ብሏል፡፡ እስካሁን ከተፈናቀሉት የተመለሱ የሉም፡፡ የቢሻንጉል ጉምዝ ክልል ለተፈናቃዮች ከ9 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡንም አሳውቋል፡፡ የቢሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ተረጋግቷል ቢልም፣ በቡለን፣በዳንጉር እና በድባጤ አሁንም የንፁሃን ግድያ እና ንብረት ውድመት አልቆመም፡፡ መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንደደረሰ አሻራ ከዚህ ቀደም ዘግቧል፡፡ በመተከል ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁሉንም ያማከለ አመራር አስፈላጊ እንደሆነ የፖለቲካ ልሂቃን ይናገራሉ፡፡ ከሱዳን ጋር ያለው የዲፕሎማሲ መሻከር ለመተከል አለመረገጋት ተጨማሪ እሳት ሊጭር ስለሚችል ሀይልን ጨምሮ ማረጋጋት አስፈላጊ ነው እየተባለ ነው፡፡ መከላከያው ለአንድ ወር የተሰጠውን የማረጋጋት ጊዜ ጨርሶ፣ከሁለት ሳምንት በኃላ መተከል በሲቪሉ እንዲመራ ይወሳል፡፡ ሲቪል አመራሩ ከሁሉም ወገን ፍትሃዊ ውክልና ከሌለው ግን አሁን የተፈጠረው ችግር ተመልሶ ሊፈጠር እንደሚችል ተፈናቃዮች ይናገራሉ፡፡ በመተከል ያሉ ተፈናቃዮች በተደጋጋሚ የመፈናቀል አደጋ የሚገጥማቸው ተገቢ ውክልና እና አግላይ መንግስታዊ መዋቅር በመኖሩ እንደሆነ ከአሻራ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሰላም እና ግጭት ባለሙያ አቶ አያና ሞላ ተናግረዋል፡፡ የመተከል ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ የሆኑት ብርጋዴር ጀኔራል አስራት ደሬፎ በታጣቂው ቡድን ነፃ ቀጠና ሆነው የነበሩ ቦታዎች በመከላከያ ቁጥጥር ውስጥ ገብተዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply