በመተከል ቡለንና ድባጤ ወረዳዎች ተፈናቅለው የሚገኙ አማራዎች አስቸኳይ መጠለያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጹ          አሻራ ሚዲያ     ህዳር 22 /2013 ዓ.ም ባህ…

በመተከል ቡለንና ድባጤ ወረዳዎች ተፈናቅለው የሚገኙ አማራዎች አስቸኳይ መጠለያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጹ አሻራ ሚዲያ ህዳር 22 /2013 ዓ.ም ባህ…

በመተከል ቡለንና ድባጤ ወረዳዎች ተፈናቅለው የሚገኙ አማራዎች አስቸኳይ መጠለያ እንደሚያስፈልጋቸው ገለጹ አሻራ ሚዲያ ህዳር 22 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር በመተከል ቡለንና ድባጤ ወረዳዎች ተፈናቅለው የሚገኙ አማራዎች ምንም አይነት መሰረታዊ የሚባል መጠለያ፤የዕለት ደራሽ ምግብ ፤ ንጹህ መጠጥ ውሃ እና መሰል ነገር እያገኙ እንዳልሆነ የመተከል አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ እጅጉ ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡ አቶ ደሳለኝ እንደሚሉት በመተከል በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች አማራዎችን ለመግደል፤ለማፈናቀልና፤ሀብት ንብረታቸውን ለመዝረፍና ለማቃጠል በሚንቀሳቀሱት የኦነግ ታጣቂዎች፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮችና ከህወሃት የስልጠናና እና የመሳሪያ ድጋፍ የሚደረግላቸው የጉሙዝ ተወላጆች ሲሆኑ አሁንም ከመግደል ሊያስቆማቸው የሚችል ሀይል አልተገኘም ፡፡ ምክት ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ህዝቡ ተደራጅቶ መሳሪያ ታጥቆ ራሱን ይከላከል የሚል መልዕክት ቢያስተላልፉም የመተከል ዞን አመራሮች አማራዎች ማስታጠቅ ሲገባቸው ለጉሙዝ ተወላጆች አራት መቶ የሚደርስ የጦር መሳሪያ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ እንደ አቶ ደሳለኝ እጅጉ ገለጻ ተፈናቃዮች በአንድ አካባቢ ሰፍረን ራሳችንን እንድከላከል አስፈላጊው ነገር ይመቻችልን የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ እያነሱ ሲሆን የዕለት ደራሽ ምግብ፤ ልብስ፤ እና መጠለያ እንዲሰራላቸው በአጽኖኦት ጠይቀዋል፡፡ ክቡራን የአሻራ ሚዲያ ተከታታዮች ከመተከል አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር ያደረግነውን ሙሉ የስልክ ቃለ ምልልስ ይዘን የምንቀርብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply