
በመተከል ቡለን በደረሰ ማንነት ተኮት ጥቃት 1 ሰው ሲገደል ግድያውን ተከትሎ ሰልፍ በወጡ ላይ መከላከያ ከባድ መሳሪያ ተኩሶ ጉዳት አደረሰ! የአማራ ሚዲያ ማእክል ሐምሌ 16 2013 አ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ትናንት ሐምሌ 15 2013ዓ.ም በቡለን ከተማ ኤማንጅ ኬላ ላይ ሽፍቶች በሰነዘሩት ጥቃት አቶ ታረቀኝ ፋሲጋ የተገደለ ሲሆን ግድያውን ተከትሎ የከተማው ህዝብ ወደ አደባባይ ሲወጣ ሰልፍ በወጣው ህዝብ ላይ መከላከያ ዲሽቃና መትረየስ ተኩሷል:: በተተኮሰው መሳሪያም:- 1.አቶ አዳሙ ባሮኖ 2.አቶ ተስፋው ገመዳ እንዲሁም ሌሎች ሁለት ንፁሀን በፀኑ ቆስለዋል:: በአሁኑ ሰዓት ቡለን ሆስፒታል ይገኛሉ :: የዘር ማፅዳት ከደረሰበት ቦታ አንዱ መተከል ነው:: ‘ቀይ’ የሚል መለያ በመስጠት ለጭፍጨፋ አዘጋጅተውታል:: በዚህም ውስጥ አማራው አገውና ሽናሻው በዋናነት ሰለባ ሆኗል:: አሁንም እንደቀጠለ ነው:: ነገር ግን የሚጮህም ሆነ የሚሰማ መንግስት የለም:: የንፁሀን ህይወት በየቀኑ ይቀጠፋል:: አይንና ጆሮ የሆኑ ጋዜጠኞች ታስረዋል:: ተቆርቋሪዋች ተሳደዋል:: ተገድለዋል:: የጉሙዝ ሽፍቶቾ በሳስማንደን ጫካ ስንቅና ትጥቅ ተሟልቶላቸው ጭፍጨፋውን በእቅድ እየፈፀሙ ነው:: ግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ የተሀድሶ ስልጠና የወሰዱ ሽፍቶች ወደ ቀደመ ስራቸው ተመልሰዋል ሲል የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ምናልባት ይታየው ገልጸዋል::
Source: Link to the Post