በመተከል ዛሬም ተጨማሪ ግድያ መፈጸሙን ነዋሪዎች ገለጹ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ03/2013 ዓም ባህር ዳር በመተከል የቁንጢ በተባለ ቀበሌ…

በመተከል ዛሬም ተጨማሪ ግድያ መፈጸሙን ነዋሪዎች ገለጹ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ03/2013 ዓም ባህር ዳር በመተከል የቁንጢ በተባለ ቀበሌ ዛሬ ታህሳስ ሶስት ቀን አራት አማራዎች በታጣቂዎች ሲገደሉ አንድ ጎጥ ውስጥ የሚገኙ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ በስልክ ገልጸውልናል፡፡ እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ በዛሬው ዕለት ታህሳስ ሰሶስት ቀን 2013 ዓ.ም በመተከል የቁንጢ በተባለ ቀበሌ የጉሙዝ ታጣቂዎች አራት ሰዎችን የገደሉ ሲሆን አንድ ጎጥ ሙሉ ቤቶችን አቃጥለዋል፡፡ በመተከል የነበረው የአካባቢው ኮማንድ ፖስትም ለጥፋቱ ተባባሪ ነው ያሉ ሲሆን የኮማንድ ፖስቱ አስተባባሪ ቶማስ ጉይ የተባለ ግለሰብ ይገኝበታል ሲሉ ገልጸውልናል፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply