በመተከል ዞን በተለያዩ አካባባዎች አሁንም አማራ /አገዎች በጉምዝ እና ኦነግ እየተገደሉ መሆናቸው ተገለፀ።           አሻራ ሚዲያ        ታህሳስ፡-30…

በመተከል ዞን በተለያዩ አካባባዎች አሁንም አማራ /አገዎች በጉምዝ እና ኦነግ እየተገደሉ መሆናቸው ተገለፀ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-30…

በመተከል ዞን በተለያዩ አካባባዎች አሁንም አማራ /አገዎች በጉምዝ እና ኦነግ እየተገደሉ መሆናቸው ተገለፀ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-30/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር በቤንሻንጉል ክልል በተለያዩ አካባባዎች አሁንም የንጹሀን ግድያ እንደቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ እንደሚታወቀው ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የአማራ ህዝብ ለረጅም ጊዜ ሲታረድና ሲጨፈጨፍ ማስቆም እንዳልቻለ ይታወቃል። ከመንግስትም ከህዝብም በኩል የክልሉ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ሲጠየቅ ቆይቷል። የክልሉ መንግስት ግን በክልሉ የሚፈፀመውን የሰው ልጆች መታረድ ከማስቆም እና ወንጀለኞች ላይ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ሃላፊነቱን እንዲወጣ የቀረበለትን ጥያቄ የራስን በራስ የማስተዳደር መብትን መጋፋት አድርጎ መውሰዱ ይታወሳል። ከምንም በላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፀረ ህዝብ ሃይሎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚነሳው ጥያቄ የክልሉን መንግስት ልብ ፍርሃት ለቆበታል። አንድ የክልል መንግስት ለህዝብ ደህንነት የሚጨነቅ ከሆነ በወንጀለኞች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ይደግፋል እንጂ በክልሉ ላይ ጦርነት እንደተከፈተ አድርጎ መውሰድ አልነበረበትም። ዳሩ ግን የክልሉ መንግስት የተሰጠውን ክልል የማስተዳደር ሃላፊነቱን ባግባቡ እንዲወጣ ባለመፈለጉ ንጹሀን አሁንም ህይወታቸው እያለፈ ነው፡፡ ይህ በክልሉ የሚፈጠረው ቀውስ በክልሉ መንግስት እንደሚደገፍ እና ለወንጀለኞችም ከለላ በመሆን የአማራ ህዝብ የዘር ፍጅት ውስጥ እጁ እንዳለበት ምንጫችን ከቦታው ነግረውናል። ከዚህ በተጨማሪም የአማራን ህዝብ በመጨፍጨፍ ላይ ያሉ አረመኔ ሃይሎችን የክልሉ መንግስት ለማስቆም ፈቃደኛ ባለመሆኑ እና የአማራ ህዝብም የሚደረገውን ጭፍጨፋ ባስቸኳይ እንዲቆም እየጠየቀ በመሆኑ የፌደራል መንግስቱ ባስቸኳይ እንዲያስቆም አለያም የአማራ ክልል መንግስት ህዝቡን ከጨፍጫፊዎች መታደግ እንዳለበት ምንጫችን ከቦታው ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ወንበራን የጥቃቱ ኢላማ ሆኗል የክልሉም የፌደራሉም መንግስት ትኩረት ነፍጎታል፡፡ በወንበራ ወረዳ በጎንዲ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተደራጀው የጉምዝ ሽፍታ ጥቃት አድርሷል። በትዕላንትናው ዕለት ብዙዎች ሲገደሉ የሰራዊቱ 1መኪና ሙሉ በሙሉ ወድሟልእንዲሁም ዲሽቃና ሌሎች መሳሪያዎችንም የጉምዝ ሽፍታዎች ዘርፈዋል። ከመከላከያ ሰራዊት አባላትና ከበጎንዲ መንገድ ፕሮጀክት ሰራተኞች ቁጥራቸው ያልታወቁ ንፁሃን ሲገደሉ ብዙ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል። የተኩስ ልውውጡም ከትላንት እስከ ዛሬ ቀጥሏል ነው የተባለው። ስለሆነም አሁንም መንግስትና የሚመለከተው አካላት ትኩረት ሰጥቶ ካልተከታተለው ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም እንዲሁም ወሎን ጨምሮ ከፍተኛ ተፈናቃይ ሊያስተናግድ ይችላል ሲሉ የመረጃ ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ገልጸውልናል ፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply