በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ለተፈናቃዮች ይሰጣል የተባለው እርዳታ በተገቢው ሁኔታ እየደረሰን አይደለም ሲሉ ተጎጅዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም…

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ለተፈናቃዮች ይሰጣል የተባለው እርዳታ በተገቢው ሁኔታ እየደረሰን አይደለም ሲሉ ተጎጅዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ የአሸባሪው የጉምዝ ታጣቂዎች ቡድን ከወራት በፊት ያደረሰውን የጅምላ ፍጅት ተከትሎ ሙሉ ሀብት ንብረቴ የተዘረፈና የተቃጠለ ቢሆንም እንደ ፈጣሪ ፍቃድ ከእነ 8 ቤተሰቦቼ ለመትረፍ ችያለሁ ሲሉ ይጀምራሉ ቅሬታ አቅራቢው አቶ ጉርሜሳ ነጋሽ። አቶ ጉርሜሳ እንደሚሉት ከተፈናቀሉ ጀምሮ ቡለን ወረዳ ወደ ማጣ ቀበሌ በመሄድ በእድሜ ከገፉ አባታቸው ቤት ተጠግተዋል። ቡለን ላይ በመንግስትና በተለያዩ በጎ ፍቃደኛ ተቋማት ካበረከቱት እርዳታ መካከል ለ2 ወራት ያህል ከማጣ ወደ ቡለን ወረዳ በመሄድ ድቄት ይወስዱ እንደነበር የተናገሩት አቶ ጉርሜሳ አሁን ላይ ግን እርዳታው ከቆመ ከአንድ ወር በላይ በመሆኑ ከእነ ቤተሰቦቸ ተቸግሬያለሁ ይላሉ። እርዳታ ይሰጠን በሚል ማጣ ቀበሌን ስንጠይቅ የእናንተ ቡለን ነው ይሉናል፤ ወደ ቡለን ስንሄድ ደግሞ ማጣ ይመጣላችኋል ይሉናል፤ በመሃል እኛ እየተራብ ነው፤ በእነሱ የአሰራር ችግር ለትራንስፖርት ወጭም እየተዳረግ ነው ሲሉ አማረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከልም በቡለን ወረዳ የእርዳታ ስርጭት ክፍል ውስጥ ይሰራሉ የተባሉትን አቶ ታሪኩን ለማነጋገር ሞክሯል። አቶ ታሪኩ ከምግብ ዋስትና በተሰጠን የተፈናቃይ መረጃ መሰረት ለሁሉም ተጎጅዎች በተቻለ መጠን እያሰራጨን እንገኛለን ብለዋል። ከሁለት ቦታ እየወሰዱ ነው የሚል ሪፖርት ስለደረሰን ለማጣራት በሚል ነው እንጅ እርዳታው እንደማንኛውም ተጎጅ የሚደርሳቸው ይሆናል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በታጣቂዎች በተደጋጋሚ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በቀላሉ በመቶዎች ሲገደሉ በሽህዎች የሚቆጠሩ በተለይም አማራዎች ተፈናቅለው ለከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መዳረጋቸው ይታወቃል። በተመሳሳይ ከበኩጅ ቀበሌ 7 ቤተሰቦቻቸው በአሸባሪው የጉምዝ ታጣቂዎች ቡድን የተጨፈጨፈባቸው አባት “እርዳታው ያለአድሎ ለምን ለተጎጅዎች አይደርስም” በማለታቸው “ብሄርን ከብሄር ሊያጋጩ ነው” በማለት በውሸት ምስክር 1 ዓመት ከ6 ወር በላይ ከተፈረደባቸው ቢቆዩም ወደ ማ/ቤት ባለመወሰዳቸው ያለማንም እረዳት በፖሊስ ጣቢያ እየተቸገሩ መሆናቸው ተገልጧል፤ መፍትሄ እንዲሰጣቸውም ተጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply