በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በዶቢ አይጋሊ ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎች በንፁሀን ላይ ግድያ ከፈፀሙ በኋላም አስከሬን ለማንሳት በሄዱ ወገኖች ላይ ተኩስ ከፈቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ህዳር 1…

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በዶቢ አይጋሊ ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎች በንፁሀን ላይ ግድያ ከፈፀሙ በኋላም አስከሬን ለማንሳት በሄዱ ወገኖች ላይ ተኩስ ከፈቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1…

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በዶቢ አይጋሊ ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎች በንፁሀን ላይ ግድያ ከፈፀሙ በኋላም አስከሬን ለማንሳት በሄዱ ወገኖች ላይ ተኩስ ከፈቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በዶቢ ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎች ህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም በንፁሀን ላይ ግድያ ከፈፀሙ በኋላም አስከሬን ለማንሳት በሄዱት ወገኖች ላይ ዛሬ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከማለዳው 2 ሰዓት ጀምሮ ተኩስ መክፈታቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል። ይህን ተከትሎም ወደ ከቡለን ወረዳ ወደ ዶቢ አይጋሊ ቀበሌ የመከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ አቅንቷል ብለዋል ነዋሪዎች። የጉምዝ ታጣቂዎች ድሪሳ መኮንን የተባሉ አባላትን ከእነ ሁለት ልጆቻቸው ጋር እንዲሁም አብሯቸው የሚኖር አንድ ቤተሰብን ጨምሮ 4 ንፁሀንን ገድለዋል። ሌሎቹ ለቀው ሲሄዱ እርስዎ ለምን ከዶቢ አይጋሊ ቀበሌ ለምን አለቀቁም በሚል ነው የሽናሻ አባት የሆኑት አቶ ድሪሳ መኮንን ከእነ ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም አብሯቸው የሚኖር አንድ የአማራ ወጣት የተገደሉት። የአቶ ድሪሳ ባለቤት እስካሁን የት እንደደረሱ ለማወቅ አልተቻለም ተብሏል። በዛሬው እለት ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም የአካባቢው ማህበረሰብ አስከሬን ለማንሳት ወደ ዶቢ አይጋሊ ቀበሌ ቢያቀናም የጉምዝ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተውባቸዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ቀደም ብሎ በሴራው ተባባሪ በሆኑ ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ አመራሮች አማካኝነት ሆንተብሎ ልዩ ልዩ ምክንያት በመፍጠር በርካታ የአካባቢው የህ/ሰብ ክፍሎች የጦር መሳሪያቸውን እንዲያወርዱ ተደርጓል። ህዳር 4ለ5 ቀን 2013 ዓ.ም ከቡለን ዶቢ ተነስተው በድባጤ በኩል ወደ ቻግኒ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ቂዶህ ላይ የጉምዝ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጭፍጨፋ ከ50 በላይ ንፁሀን በግፍ መገደላቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎም በማግስቱ በቡለን ወረዳ በፀጥታ አካላት ከተያዙት መካከል የህወሀት ተልዕኮ አስፈጻሚ በሚል ሻምበል መብራቱ የተባለ በሜድሮክ ውስጥ የሚሰራ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል። በቤቱ ውስጥ በተደረገ ፍተሻም ከ100 ሲም ካርድ በላይ በቤቱ ውስጥ መገኘቱንና ከጎኑም 20 የጥፋት ተባባሪዎች እንዳሉና ከ7 ያላነሱ የቤጉ አመራሮች እጅ ጭምር እንዳለበት ስለማጋለጡ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የኦነግ ሸኔም አዋሳኝ በሆነው በምዕራብ ወለጋ አድርጎ በድባጤ ወረዳ አልባሳና ሙዘን፣ እንዲሁም በቡለን ኤጳር በኩል በመግባት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከጉምዝ ታጣቂዎች ጋር አብሮ በመስራት ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እየፈፀመ መሆኑም ተገልጧል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሀብት ንብረት የተዘረፈባቸውና እርዳታ ፈላጊ ተፈናቃዮችም በቡለን የወረዳ አዳራሽ ተጠልለው እንደሚገኙና ሌሎች በርካታ ተፈናቃዮችም ወደየቤተሰባቸው የተጠጉ መሆናቸው ተጠቁሟል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply