በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ  የጉምዝና የኦነግ  ታጣቂዎች ንብረት ለመዝረፍ ሲሉ  ንጸሀንን አማራዎችን  በጥይት በመምታት ማቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ተናገሩ።…

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የጉምዝና የኦነግ ታጣቂዎች ንብረት ለመዝረፍ ሲሉ ንጸሀንን አማራዎችን በጥይት በመምታት ማቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ተናገሩ።…

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የጉምዝና የኦነግ ታጣቂዎች ንብረት ለመዝረፍ ሲሉ ንጸሀንን አማራዎችን በጥይት በመምታት ማቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ተናገሩ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡- 20/04/13/ ዓ.ም ባህር ዳር ከትሕነግ ጋር የወገኑት፣ የጉምዝ እና የኦነግ ታጣቂዎች ለዘር ማጥፋት ተግባሩ ዋና ተዋኒያን ይሁኑ እንጅ የመንግስት አካላትም እየተባበሩ መሆናቸው በተለያዩ ጊዜያት እና በተለያዩ ወገኖች ሲገለጽ ቆይቷል።ይህን ደግሞ አሻራ ሚዲያ ለህዝብ ሲያድርስ መቆየቱ ያታወሳል፡፡ የኦነግና የጉምዝ ታጣቂዎች ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ያደረሱት ጭፍጨፋ ሳይዘነጋ ከሳምንታት በፊት በድባጤ ወረዳ በአልባሳ፣ሙዘን፣ገፈሪ፣ቆርቃና የተለያዩ ቀበሌዎች በሚኖሩ አማራዎች ላይ ተባብረው የጅምላ እልቂት መፈፀማቸው አላረካቸውም። ከሰሞኑ የጉምዝ ታጣቂዎች ከቤንሻንጉል ክልል አመራሮች ጋር ከሀሳብ እስከ ትጥቅና ስንቅ አቅርቦት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በመተባበር በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ በዋናነት አማራ ላይ የጅምላ ፍጅት ማድረሳቸው ይታወሳል። በትዕናንትናው ዕለትም ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ደግሞ ከሳስማንደን ቀበሌ የቁም ከብቶችን ዘርፈው ለማምለጥ ሁለት አማራዎችን በጥይት እና በቀስት በመምታት አቁስለዋል ነው ያሉት ነዋሪዎቹ። በመጨረሻም መንግስት በከሃዲው ትህነግ ላይ የወሰደውን እርምጃ በመተከልና በወለጋ በመድገም ሰው ሆነው የሰው ስጋ እስከ መብላት የደረሱ ጨካኝና አጥፊውን ቡድን አደብ የማስገዛት ብሎም ህዝብንና ሀገርን የማዳን ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply