በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የጉምዝ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ የሰው ህይወት ማለፉ እና የቆሰለ ስለመኖሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም           አ…

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የጉምዝ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ የሰው ህይወት ማለፉ እና የቆሰለ ስለመኖሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አ…

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የጉምዝ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ የሰው ህይወት ማለፉ እና የቆሰለ ስለመኖሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ዶቢ ቀበሌ አይጋሊ በተባለ አካባቢ በሽብር ተግባር የተሰማሩ የጉምዝ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ነዋሪዎች እንደሚሉት 4 ሰዎች ተገድለዋል፤ የቆሰሉም አሉ። ዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 3 ሰዓት ላይ በከፈቱት ተኩስ የቀበሌ ሸንጎ የሆኑትን መገርሳ ታደሰን ጨምሮ 4 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሰቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል። በርካታ ቤቶችና አዝመራም የተቃጠለ መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎች በዋናነት አማራ ላይ ያተኩሩ እንጅ ቀይ የሆኑትን ሁሉንም እያሳደዱ ነው ብለዋል። ነዋሪዎች ሲቀጥሉ በተለያዩ ጊዜያት ያፈናቀሏቸው አማሮች በዶቢ ቀበሌ እንደሚገኙ ስለሚያውቁ በአይጋሊ ጀምረው ሁሉንም በማስለቀቅ ዶቢን ለመቆጣጠር እቅድ እንዳላቸው ሰምተናል ብለዋል። አይጋሊ አካባቢ ከ600 በላይ የሚሆኑ የነፍሰ ገዳዩ የጉምዝ ታጣቂዎች ቡድን መሽጎ እንደሚገኝ የተጠቆመ ሲሆን በዶቢ እና በአካባቢው የሚገኙ የመንግስት ታጣቂዎች እና አርሶ አደሩ አሁን ላይ የአፀፋ ምላሽ እየሰጠ መሆኑ ተገልጧል። የቡለን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛት ነሲ በዶቢ አይጋሊ መስመር ላይ የጉምዝ ታጣቂዎች በአካባቢው ሚሊሾች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን አረጋግጠዋል። የተወሰነ የቆሰለ ሰው አለ የሚል መረጃ ስለደረሰን ተጨማሪ የፀጥታ ሀይል ጨምረን አምቡላንስ ልከናል፤ የኔት ወርክ ችግር ስላለ የተገደሉና የቆሰሉትን በተመለከተ ሲጣራ መረጃ እንሰጣለን ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply