በመተከል ዞን አልመሃል የሚገኝ የአሸባሪው ህወሃት ሠራዊት ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ወደመ‼️ መስከረም 21 ቀን 2014 አሻራ ሚዲያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አልመሃል ቀበሌ ልዩ…

በመተከል ዞን አልመሃል የሚገኝ የአሸባሪው ህወሃት ሠራዊት ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ወደመ‼️ መስከረም 21 ቀን 2014 አሻራ ሚዲያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አልመሃል ቀበሌ ልዩ ስሙ ሽንኩር መንደር የሚገኝ የአሸባሪው ህወሃት ሠራዊት ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ወውደሙን የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ገልጸጰጿል። በዚህም 47 የጠላት አሸባሪዎች መደምሰሳቸውን በአካባቢው የሚገኝ ሠራዊት አመራር ሻለቃ ዮሀንስ እውነቱ ተናግረዋል ፡፡ እንደ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሩ ገለፃ ከሆነ በተደረገው አሰሳ የተለያዩ ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ማለትም 8 ፀረ-ተሸከርካሪ ፈንጅ እና 1 መገናኛ ራዲዮ የተያዘ ሲሆን ፤ 2 የጠላት ሞተር ሳይክል እና የህውሀት ሠራዊት ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በሌላ በኩል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሰዳል …ወረዳ የጉሙዝ ታጣቂዎች ከመስከረም 14 ጀምሮ ሕጸናትም፣ አረጋውያንን እና ሴቶችን ጨምሮ 145 ገደማ የጉሙዝ ተወላጆችን ማገታቸውን እና ቢያንስ ሁለቱን እንደገደሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። ታጣቂዎቹ ሰዎቹን ያገቷቸው “ዓላማችን አልደገፋችሁም” በማለት እንደሆነ ከእገታው ያመለጡ ሰዎች ተናግረዋል። ከወሩ አጋማሽ ጀምሮ ከ5 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ኮሚሽኑ ጠቁሞ፣ ከመስከረም 16 ጀምሮ ጸጥታ ኃይሎች ከታጣቂዎች ጋር ውጊያ ላይ መሆናቸውን አመልክቷል። በመተከል እና ካማሺ ዞኖች የነዋሪዎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚወሰዱ ርምጃዎች ፈጣን እና ዘላቂ እንዲሆኑ ኮሚሽኑ አክሎ አሳስቧል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply