በመተከል ዞን ከተፈፀመው ዘር ተኮር ጥቃትና ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆኑን የቤንሻንጉል ከልል ኮምንኬሽን ቢሮ  ያወጣው መግለጫ ትክ…

በመተከል ዞን ከተፈፀመው ዘር ተኮር ጥቃትና ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆኑን የቤንሻንጉል ከልል ኮምንኬሽን ቢሮ ያወጣው መግለጫ ትክ…

በመተከል ዞን ከተፈፀመው ዘር ተኮር ጥቃትና ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆኑን የቤንሻንጉል ከልል ኮምንኬሽን ቢሮ ያወጣው መግለጫ ትክክለኛነት እንደሚጎድለው የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-15/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት በመተከል ዞን ከተፈፀመው ዘር ተኮር ጥቃትና ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ከፍተኛ እና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ሥር ማዋል ጀምሪያለሁ ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮ ጽሕፈት ቤት አስፍረዋል፡፡ በዞኑ በተፈፀመው ዘር ተኮር ጥቃትና ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበትን፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝ መግለጹ ይታወሳል፡፡፡፡ በዚህም መሠረት ፡- 1ኛ. አቶ ቶማስ ኩዊ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ 2ኛ. አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር 3ኛ. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፡- የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር 4ኛ. አቶ ባንዲንግ ማራ፡- የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ 5ኛ. አረጋ ባልቢድ፡- የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩ ቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ነው የተነገረው፡፡ ይሁን እንጅ እኛም በመተከል ከሚገኙ የመረጃ ምንጮቻችን ጋር ባደረግነው የስልክ ልውውጥ ከዚህ በፊትም መሰል መግለጫዎች እንደሚሰጥ ጠቁመው ተያዙ ስለሚባሉ አመራሮች ከማህበራዊ ሚዲያ ውጭ ምንም አሳማኝ የሆነ ነገር እንደሌላቸው ነው የተናገሩት፡፡ እንደምንጫችን ገለጻ ተያዙ የሚባሉ ሰዎች ለጭፍጨፋው ዋና ተዋኒያን የሆኑ የክልሉ አመራሮችን ሽፋን ለመሥጠት የተደረገ ነው እንጅ ለግድያውና ለጭፍጨፋው ዋና ተባባሪ የሆኑና ትዕዛዝ ሰጭ የሆኑ የቤንሻንጉል ክልል ከፍተኛ አመራሮች አሁንም በሥልጣን ላይ አሉ ብለዋል፡፡ በመሆኑም በቤንሻንጉል ከልል ኮምንኬሽን ቢሮ የተላለፈው መግለጫ ትክክለኛነት የጎደለው ነው ሲሉ ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም መንግስት እርምጃ መውሰድ ካለበት ከቀበሌ አመራሮች እስከ ክልል አመራሮች ድረስ መሆን አለበት ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply