You are currently viewing በመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት በቁጥጥር ስር ከዋሉት 35 የአማራ የጸጥታ አካላት መካከል 11 ልዩ ኃይሎች ሲፈቱ 24ቱ ገና አልተፈቱም ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 2 ቀን 2…

በመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት በቁጥጥር ስር ከዋሉት 35 የአማራ የጸጥታ አካላት መካከል 11 ልዩ ኃይሎች ሲፈቱ 24ቱ ገና አልተፈቱም ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2…

በመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት በቁጥጥር ስር ከዋሉት 35 የአማራ የጸጥታ አካላት መካከል 11 ልዩ ኃይሎች ሲፈቱ 24ቱ ገና አልተፈቱም ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ገነተ ማርያም ከተማ የተደራጀውና የታጠቀው የጉምዝ ሽፍታ ቡድን 3 ንጹሃንን መሀል ከተማ በጠራራ ጸሀይ መግደሉን ተከትሎ ከተወሰደው የአጸፋ እርምጃ ጋር በተያያዘ በሚል 35 የአማራ የጸጥታ አካላት ህዳር 1 ቀን 2014 መታሰራቸው ይታወሳል። በመተከል ኮማንድ ፖስት በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል 22ቱ የአማራ ልዩ ኃይል ሲሆኑ 13 ደግሞ በማንዱራ የሚኖሩ የአማራ ሚሊሻዎች ናቸው። ህዳር 2 ቀን 2014 ረፋድ ላይ ሁሉም ልዩ ኃይሎችን ከእስር ቤት ሲወጡ የተመለከቱ ምንጮች የህዝቡን ቅሬታ እና ቁጣ ሰምተው ለቀዋቸዋል ያሉ ቢሆንም ከመካከላቸው 11ዱ አልተፈቱም። በአጠቃላይ 11 የአማራ ልዩ ኃይል አባላትና 13 የአማራ ሚሊሻ አባላት በድምሩ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ 24 የአማራ የጸጥታ አካላት በእስር ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። የመተከል ኮማንድ ፖስት ከአጸፋ እርምጃው ጋር በተያያዘ ይህን ያህል የጸጥታ አካላትን ወደ እስር ማጋዙን ተከትሎ ነዋሪዎችም ሆነ የጸጥታ አካላት ተቆጥተዋል፤ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥም ጠይቀዋል፤ በየቦታው በጅምላ እየተጨፈጨፈ በእስካባተር ሲቀበር የከረመውም ሰው መሆኑ መታወቅ አለበት ብለዋል። ይህን ክፍተት የተመለከተው ጠላትም ሌሊት ላይ በማንዱራ የቡድን መሳሪያ ጭምር ሲተኩስ ማደሩ ተሰምቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply