You are currently viewing በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች አማራ ተኮር ጥቃቱ እንደቀጠለ ነው፤ ከሰሞኑ በማንዱራ እና በድባጤ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ከ7 በላይ አማራዎች በኦነግ ሸኔ እና በጉሙዝ የሽፍታ ቡድን ተገድ…

በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች አማራ ተኮር ጥቃቱ እንደቀጠለ ነው፤ ከሰሞኑ በማንዱራ እና በድባጤ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ከ7 በላይ አማራዎች በኦነግ ሸኔ እና በጉሙዝ የሽፍታ ቡድን ተገድ…

በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች አማራ ተኮር ጥቃቱ እንደቀጠለ ነው፤ ከሰሞኑ በማንዱራ እና በድባጤ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ከ7 በላይ አማራዎች በኦነግ ሸኔ እና በጉሙዝ የሽፍታ ቡድን ተገድለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች አማራ ተኮር ጥቃቱ እንደቀጠለ መሆኑ ተገለጸ፤ ከሰሞኑ በማንዱራ እና በድባጤ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ከ7 በላይ አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በጉሙዝ የሽፍታ ቡድን ተገድለዋል። 1) በማንዱራ ወረዳ በእርሻ ማሳቸው ላይ በአጨዳ ስራ ላይ የነበሩ ሁለት፣ በከብት ጥበቃ ላይ የነበረ አንድ በድምሩ 3 አማራዎች በጥይት ተገድለዋል። ግድያው የተፈጸመውም በጉሙዝ የሽፍታ ቡድን ነው። 2) በእለተ ረቡዕ ህዳር 14/2015 ዓ/ም እኩለ ቀን አካባቢ ደግሞ በድባጤ ወረዳ ሳስማንደን ቀበሌ አንድ የባጃጅ ሾፌር እና በባጃጁ ውስጥ የነበሩ 2 ሰዎች በድምሩ 3ቱም በጉሙዝ የሽፍታ ቡድን ጥይት እና በስለት በግፍ ተገድለዋል። 3) በድባጤ ወረዳ በቆርቃ እና በጋሌሳ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዲምቱ በተባለ ተራራ አካባቢ ደግሞ የቆርቃ ቀበሌ ት/ቤት እና ጤና ጣቢያ በሌሊት ተዘረፈ መባሉን ተከትሎ ረፋድ ላይ በመኪና እየተጓዙ ሳለ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በተከፈተባቸው ጥቃት ከ15ቱ መካከል 1 ሚሊሻ ሲገደል 9 የቆሰሉ መሆናቸውን ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ሚሊሾቹም “ትምህርት ቤቱንና ጤና ጣቢያውን እየዘረፈው ያለው “ኦነግ ሸኔ” በመሆኑ መከላከያ ወደ አካባቢው እንዲገባ አድርጉ፣ የቡድን መሳሪያ ለታጠቀ አካል ኋላቀር መሳሪያ አሲይዛችሁ እኛን አትላኩን” ብለው ቅሬታ በማንሳታቸው የተበሳጩ የመስተዳድር አካላት “ኦነግ ሸኔ እያላችሁ የኦሮሞን ስም ለምን ታጠለሻላችሁ” በማለት አስገድደው እንደወሰዷቸውና በመካከል ጥቃት መፈጸሙ ነው የተገለጸው። በእለቱ በተፈጸመው ጥቃት የተገደለውም የኑስ የሱፍ የተባለ ሚሊሻ ነው። ከቆሰሉት ሚሊሾች መካከልም:_ 1) ዘለቀ አበራ_ በሁለት ጥይት ተመቶ በከባድ የቆሰለ ሲሆን 2) ድሪባ ገመዳ የተባለ ሚሊሻም እጁን የተመታ መሆኑ ታውቋል። በቆርቃ እና አካባቢው የነበሩ መምህራንና ሀኪሞችም በጥቃቱ ምክንያት ከሌሊቱ 7 ሰዓት ጀምሮ ወደ ጋሌሳ ቀበሌ ሸሽተው መግባታቸው ታውቋል። በመጨረሻም አርሶ አደሩ ሰብሉን በአግባቡ እንዳይሰበስብ እንዲሁም ተማሪዎችም ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች በአካባቢው መከላከያ በአስቸኳይ እንዲገባላቸው ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply