በመተከል ዞን የተጀመረው ህግ የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ‼️ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ ) በቀጠናው የተጀመረው ህግ የማስከበር ተግባ…

በመተከል ዞን የተጀመረው ህግ የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ‼️ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ ) በቀጠናው የተጀመረው ህግ የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል። የከተማ ነዋሪዎች በቀጠናው ተሰማርቶ የሚገኘውን ሰራዊት የሚደግፍና በዞኑ የሚገኘውን አጥፊ ቡድን ደግሞ የሚያወግዝ ሰልፍ በከተማዋ አደባባይ ሰልፍ አካሂደዋል። የመተከል ዞንን ሰላም ለመመለስ ተሰማሮቶ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌድራል ፖሊስ፣ የየክልሉ ልዩ ኃይሎችና፣ ሚሊሻ አባላትን የጀመሩትን ህግ የማስከበር ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ነዋሪዎች በድጋፍ ሰልፉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የህወሓትን ሴራ ተቀብለው ቀጠናውን እያተራመሱ የሚገኙ የጉሙዝ ብሄረሰብን እንደማይወክል የብሄረሰቡ ተወላጆች በድጋፍ ሰልፉ ላይ ድምጻቸውን አሰምተዋል። በድጋፍ ሰልፉ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የግልግል በለስ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብታሙ ውባልታ እንዳሉት ንጹሃን የጉሙዝ ብሄረሰብን ሽፋን በማድረግ ቀጠናውን እያወኩ የሚገኙ አጥፊዎችን ከማህበረሰቡ በመለየት እየተወሰደ ያለው ህግን የማስከበር ተግባርን ለማበረታታት ያሳያችሁትን ድጋፍ አጠናክራችሁ በማስቀጠል ለሰላም ዘብ መቆም አለባችሁ ብለዋል። ለዘመናት የጋራ ዕሴት መስርተው ሲኖሩ የነበሩ ህዝቦችን የብሄር ታርጋ በመለጠፍ የእርስ በእርስ ግጭት በመፍጠር ቀጠናው እንዳይረጋጋ የሚፈልጉ ሃይሎችን ለማስወገድ በሚደረግረ ጥረት ህብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ የ7ኛ ሜካናይዝድ ጦር ዋና አዛዥና የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ተወካይ ኮሎኔል በስፋት ፈንቴ ተናግረዋል። በዞኑ ህግን ለማስከበር የተጀመረው ኦፕሬሽን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ኮሎኔሉ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለምንም ስጋት ለማጠናቀቅ ሰራዊቱ ሁልጊዜ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑን ተናግረዋል። የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በበኩላቸው የኢትዮጵያን እድገት የማይፈልጉ ኃይሎች ሲፈልጉ በሃይማኖት፣ሲያሻቸው በብሄር ሲቀጥልም በጎሳ በመከፋፋል ሲሰራ የነበረው ሴራ በመገንዝብ ሽፍታውን ቡድን ለማጥፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማድረግ ከወጣቱ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን አሳስበዋል። ሽፍታው ቡድን የጉሙዝ ብሄረሰብን አይወክልም፣ ሽፍታ ሀገር አይመራም፣ የተጀመረው ኦፕሬሽን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፣ የጁንታው ተላላኪ አጥፊዎችን መንግስት በአጭር ጊዜ እርምጃ ሊወስድ ይገባል የሚሉት በድጋፍ ሰልፉ የተንጸባረቁ መልዕክቶች ናቸው። መተከል ዞን ኮሙኒኬሽን ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply