በመተከል ዞን የጉምዝ ታጣቂዎች ሰብል በመሰብሰብ ላይ ያሉ አማራዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተሰማ።    (አሻራ፣ጥር 19/2013ዓ•ም ባህርዳር) በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ አይቃሽ ቀበሌ በሰ…

በመተከል ዞን የጉምዝ ታጣቂዎች ሰብል በመሰብሰብ ላይ ያሉ አማራዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተሰማ። (አሻራ፣ጥር 19/2013ዓ•ም ባህርዳር) በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ አይቃሽ ቀበሌ በሰ…

በመተከል ዞን የጉምዝ ታጣቂዎች ሰብል በመሰብሰብ ላይ ያሉ አማራዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተሰማ። (አሻራ፣ጥር 19/2013ዓ•ም ባህርዳር) በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ አይቃሽ ቀበሌ በሰብል ስብሰባ ላይ የነበሩ አማራዎች ላይ የጉምዝ ታጣቂዎች ተኩስ መክፈታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል። ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ በአርሶ አደሮች ላይ በተከፈተ ተኩስ አቶ ውብነህ ሞላ የተባሉ ሰው መገደሉን እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ነዋሪዎቹ ገልፀውልናል። በመተከል ለሚፈፀመው ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሊቆም ያልቻለው በየደረጃው ያሉ የቤኒሻንጉል ክልል የመንግስት መዋቅር እጅ ስላለበት ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክርቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታደለ ተረፈ በግለፃቸው ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply