“በመተከል ዞን ያለ አማራ ለገዳይ አደራ የተሰጠ ህዝብ እንደሆነ አድርጌ እቆጥረዋለሁ!” የመተከል ነዋሪ ከተናገረው! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ…   ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም…

“በመተከል ዞን ያለ አማራ ለገዳይ አደራ የተሰጠ ህዝብ እንደሆነ አድርጌ እቆጥረዋለሁ!” የመተከል ነዋሪ ከተናገረው! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ… ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም…

“በመተከል ዞን ያለ አማራ ለገዳይ አደራ የተሰጠ ህዝብ እንደሆነ አድርጌ እቆጥረዋለሁ!” የመተከል ነዋሪ ከተናገረው! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ… ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ “በመተከል ዞን ያለ አማራ ለገዳይ አደራ የተሰጠ ህዝብ እንደሆነ አድርጌ እቆጥረዋለሁ!” ያለው የአካባቢው ነዋሪ በመተከል ነገሮች ሁሉ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆኑ ነው ይለናል። “መከራና ስቃይ፣ ሞትም ይለመዳል ወይ!” ብለህ እንድትጠይቅ ትገደዳለህ ያለው ነዋሪው “እነሱ የመግደል ፍቃድ ያላቸው እኛም የመገደል ግዴታ ያለብን” እስኪመስል ድረስ ነው ያለው ሁኔታ ሲልም አክሏል። አማራን ብዙ ጊዜ ጮኸናል፣የደም እምባ አልቅሰናል ግን ፍትህ አላገኘንም ያለው ምንጫችን የቤንሻንጉል ጉምዝ፣ የአማራም ሆነ የፌደራል መንግስት የማያውቀን የባይተዋር ህዝብ ሆነናል ነው ያለው። ከሙዘን ቀበሌ 7 ቤተሰቦቿን በነፍሰ ገዳዮች ያጣች ህጻን ከማን ጋር እንደ ምትጠጋ ግራ የገባት፣ አገውኛ የሚናገር ልጅ ሌላ ቋንቋ የማይችል ሁሉን ቤተሰቦቹን አጥቶ ከማን ጋር ለመግባባት ግራ እስኪገባው ድረስ እጅግ ቀፋፊ፣ አሳፋሪና አስፈሪ የሆነ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ስለመሆናቸው ገልጧል። በመተከል ዞን ባሉ 7 ወረዳዎች ላይ በተለያዩ ጊዜያት በእቅድ የተመራ፣በደንብ የተደራጀና ቀድሞ ግብአት በተዘጋጀለት መልኩ አማራን ለይቶ ዘር የማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞበታል። በሽህ የሚቆጠሩ ከሞት የተረፉ የአማራ ተፈናቃዮች በአግባቡ መጠለያ ወይም ድንኳን እንዲዘረጉ እንኳ አልተፈቀደላቸውም፤ አይደለም መልሶ ለማቋቋም በቂ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ እንኳ አልተቻለም ሲል ገልጧል። የተገደሉት፣የቆሰሉትና የተፈናቃዮችን ቁጥር ሆነብሎ በማጣረስና በመደበቅ ተግባር ላይ የተጠመደው መንግስት እንዲበተኑ ስለሚፈልግ መጠለያ እንኳ አልሰራላቸውም፤ ስደተኞችን እየተቀበለች ያለች አገር ኢትዮጵያ ዜጎቿ ሜዳ ላይ ሲበተኑ ዴንታ ቢስ ሆና ማየት እንደሚሰማው አስታውቋል። ቤጉ መዋቅር ውስጥ ያሉ በርካታ ሰዎች የትሕነግና የኦነግ ፈረሶች መሆናቸው ይታወቃል ያለው ምንጫችን ሰው አርደው ኩላሊት የሚበሉ ሰዋዊ አውሬዎች እንዳሉ ግልፅ መሆን እንዳለበትም ጠቁሟል። ከአሁን በኋላ ለመተከል ችግር መፍትሄው የሰሜኑን ኦፕሬሽን ያለምንም መወላወል መተግበር ስለመሆኑም አስረግጦ ተናግሯል። በድምፅ የታገዘ ሙሉ ዝግጅቱን (ክፍል 1 እና 2) በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply