በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንጹኃን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲያደርሱ ከነበሩት ውስጥ 16 ሽፍቶች ተደመሰሱ

በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንጹኃን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲያደርሱ ከነበሩት ውስጥ 16 ሽፍቶች ተደመሰሱ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንጹኃን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲያደርሱ ከነበሩት ውስጥ 16 ሽፍቶች ተደምስሰዋል፡፡
ሽፍቶቹ የተደመሰሱት በአካባቢው ዘላቂ ሠላምን ለማምጣት እየሠሩ የሚገኙት የሀገር መከላከያ፣ የፌዴራል ፖለስ እና የክልሉ የጸጥታ ኃይል በወሰዱት እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
በመተከል ዞን በተለይም የሕወኃትን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብሎ በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት እያደረሰ የሚገኘውን የጸረ-ሠላም ኃይል ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ እና አካባቢውን ወደ ዘላቂ ሠላም ለመመለስ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንጹኃን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲያደርሱ ከነበሩት ውስጥ 16 ሽፍቶች ተደመሰሱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply