በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ከማምቡክ ከተማ በቅርብ ርቀት የጉምዝ ታጣቂዎች ካገቷቸው 12 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች መካከል የአማራ ተወላጆችን ለይተው ማስቀረታቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ከማምቡክ ከተማ በቅርብ ርቀት የጉምዝ ታጣቂዎች ካገቷቸው 12 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች መካከል የአማራ ተወላጆችን ለይተው ማስቀረታቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ከማምቡክ ከተማ በቅርብ ርቀት የጉምዝ ታጣቂዎች ካገቷቸው 12 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች መካከል የአማራ ተወላጆችን ለይተው ማስቀረታቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ከዳንጉር ወረዳ ማምቡክ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ቁጥር 3 በተባለች የገጠር ቀበሌ አካባቢ ባለጫካ ትናንት ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት በመኪና ሲጓዙ በነበሩ የጤና ባለሙያዎች ላይ ተኩስ የከፈቱ የጉምዝ ታጣቂዎች ባለሙያዎችን አግተው ወስደዋል። በዳንጉር ከጉብላክ ጤና ጣቢያ በጉምዝ የልዩ ሀይል አባላት አጃቢነት በመኪና ተጭነው ወደ ማምቡክ እየተጓዙ የነበሩ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር 3 አካባቢ ሲደርሱ ነው ተኩስ የተከፈተባቸው ተብሏል። በወቅቱም ከልዩ ሀይሎች መካከል ከፊሎቹ ከጨፍጫፊ የጉምዝ ታጣቂዎች ጋር የተቀላቀሉ ሲሆን ግማሹ ለመከላከል ሙከራ ማድረጋቸውንና የተገደለም እንዳለ የገለፁት የአካባቢው ነዋሪ ሾፌሩን ጨምሮ 12 የጤና ባለሙያዎችን አፍነው እንደወሰዱ አስታውቀዋል። ትናንት ማታ 4:30 ሰዓት እና ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ማለዳ ሾፌር ቶሎሳን ጨምሮ ሌሎች ማንነታቸው ተለይቶ የተለቀቁ ሲሆኑ ከታገቱት መካከልም ቁጥራቸው ከ5 እስከ 6 የሚደርሱ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጤና ባለሙያዎች በማንነታቸው ብቻ ተለይተው ከእገታ እንዳልተለቀቁ ነው የአካባቢው ነዋሪ የተናገሩት። እንደአብነትም ሜሮን አለሙ፣ብዙአየሁ ማማሩ፣አቡኔ ሽፈራው፣ማዕዶት ይሁኔና ገዛህኝ ጎነጠ የተባሉ ባለሙያዎች አማራ በመሆናቸው ተለይተው እስከ ዛሬ አልተለቀቁም ነው የተባለው። አጋቾች በማንዴሶ በርሀ እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል ያሉት ምንጫችን የአማራ ክልል መንግስት ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ወይም ከመተከል ዞን ጋር በመነጋገር በጥምረት ቢሰሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚችሉ ጠቁመዋል። በተያያዘ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ትናንት ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም በድባጤ ወረዳ በጎንጎ ቀበሌ የአቶ ተሻለ በቀለ እና የአቶ ታምር ጎመራውን መሳሪያ በኃይል ነጥቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply