በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ሰምቦ ስሬ ቀበሌ በ30 ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ አማራዎች በኦነግ ሸኔዎች እንዲፈናቀሉ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ሰምቦ ስሬ ቀበሌ በ30 ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ አማራዎች በኦነግ ሸኔዎች እንዲፈናቀሉ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ሰምቦ ስሬ ቀበሌ በ30 ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ አማራዎች በኦነግ ሸኔዎች እንዲፈናቀሉ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ሰምቦ ስሬ ቀበሌ በ30 ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ አማራዎች በኦነግ ሸኔዎች በዛሬው እለት ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። “ሌሎች ሲለቁ እናንተ እስካሁን ድረስ እንዴት ተቀመጣችሁ” በሚል በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ድብደባ፣ማስፈራሪያና ዛቻ ሲፈፀምባቸው ነው ዓመቱን ሁሉ የደከሙበትን ምርታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ ንብረታቸውን ጥለው ዛሬ አመሻሹን ለቀው ወደ ጋሌሳ ቀበሌ የገቡት። አንዳንዶችን አንበርክከው እንደገረፏቸውና “ዛሬ ካልወጣችሁ ነገ ከ11 ሰዓት በኋላ በጥይት ትመታላችሁ!” በማለት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እንዳስጠነቀቋቸው ነው ከሰምቦ ስሬ ቀበሌ ተፈናቅለው የወጡት። በአንዳንድ በጎ ሰዎች ልመና ከግድያ ተርፈው ሙሉ ሀብት ንብረታቸውን ለአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጥለው ለመውጣት ተገደዋል። በመተከል ድባጤ ወረዳ ሰምቦ ስሬ፣ቆርቃና ጎንጎ ቀበሌዎች በበላይነት በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚታመሱ ቀበሌዎች ናቸው። ከሙዘን፣ከአልባሳና ከገፈሪ ቀበሌዎች በማንነታቸው ምክንያት ብቻ የተፈናቀሉ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች በሚገኙበት ጋሌሳ ቀበሌ ኦነግ ሸኔ ህዳር 6ለ7 ቀን 2013 ዓ.ም በምሽት ገብቶ እስረኛ አስፈትቶ ከመውሰዱ በተጨማሪ፣ የቀበሌ፣የፖሊስና የብድርና ቁጠባ ተቋማት ሰነዶችን ማውደሙ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply