በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በቆርቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት እና ከአንዲት የኦሮሞ ተወላጅ ጋር ተጋብተው በርካታ ልጆችን ያፈሩት አቶ እሱባለው አሸብር በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ። አ…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በቆርቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት እና ከአንዲት የኦሮሞ ተወላጅ ጋር ተጋብተው በርካታ ልጆችን ያፈሩት አቶ እሱባለው አሸብር በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ። አ…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በቆርቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት እና ከአንዲት የኦሮሞ ተወላጅ ጋር ተጋብተው በርካታ ልጆችን ያፈሩት አቶ እሱባለው አሸብር በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የቆርቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት በማንነታቸው አማራ የሆኑት አቶ እሱባለው አሸብር ከኦሮሞ ተወላጅ ጋር ተጋብቸ በርካታ ልጆችን አፍርቻለሁ አይነኩኝ በሚል ከቀያቸው አልለቀቁም። ይሁን እንጅ ዘር አጥፊው የኦነግ ሸኔ ቡድን አማራ ሁሉ ከቆርቃ ሲለቅ ለምን እሱስ አይለቅም በሚል በተደጋጋሚ እንዲለቅ ማስፈራራቱን ቀጠለ። ከሃዲውና በታኙ የኦነግ ሸኔ ቡድን በእለተ እሁድ ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ መኖሪያ ቤቱ በማቅናት ገና መረጃ አሳልፎ ይሰጡ ይሆናል በሚል በጥይት የገደሏቸው መሆኑን ነው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለከተው። ጨፍጫፊው ቡድን እስካሁን በመተከል ዞን የሚገኙ 6 የሚሆኑ ቀበሌዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ነው ምንጮች እየተናገሩ ያሉት። ጎንጎ፣ ቆርቃ፣ ሰምቦ ስሬ፣ ሙዘን፣አልባሳና ገፈሪ እንዲሁም ከዳለቲ ጨሊያን በበላይነት ተቆጣጥረው የትምህርት፣ የህክምና እና መሰል አገልሎቶች ሁሉ እንዳይሰጡ በማድረግና በቀጥታ የአማራን ዘር እያጠፉ መሆኑ ተገልጧል። መንገድ ላይ ኬላ በመጣል ሳይቀር ወደ ገበያ የሚሄዱ የአካባቢው ነዋሪዎችን እንደሚፈትሹ፣ አማራውን ለይተው እንደሚመልሱትና የፈረዱበትንም እንደሚገድሉ ነው የደረሰን መረጃ ያመለከተው። ጉዳዩን ለማጣራት በሚል የድባጤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛት ነሲን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ስልካቸው ባለመስራቱ ለጊዜው አልተሳካም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply