በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በዝግህ ቀበሌ በእርሻ ማሳቸው ላይ በጉምዝ ታጣቂዎች አፈና የተደረገባቸው ከ50 በላይ አርሶ አደሮች በመከላከያ ትብብር ያለምንም ጉዳት ከከበባ አመለጡ። አማራ ሚዲያ…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በዝግህ ቀበሌ በእርሻ ማሳቸው ላይ በጉምዝ ታጣቂዎች አፈና የተደረገባቸው ከ50 በላይ አርሶ አደሮች በመከላከያ ትብብር ያለምንም ጉዳት ከከበባ አመለጡ። አማራ ሚዲያ…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በዝግህ ቀበሌ በእርሻ ማሳቸው ላይ በጉምዝ ታጣቂዎች አፈና የተደረገባቸው ከ50 በላይ አርሶ አደሮች በመከላከያ ትብብር ያለምንም ጉዳት ከከበባ አመለጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ዝግህ በተባለ ቀበሌ በእርሻ ማሳቸው ሆነው የደረሰ ሰብላቸውን በመሰብሰብ ላይ ያሉ ከ50 በላይ አርሶ አደሮች በጉምዝ ታጣቂዎች ከበባ የተደረገባቸው መሆኑን በመግለፅ መንግስት እንዲደርስላቸው ስለመጠየቃቸው የአማራ ሚዲያ ማዕከል መዘገቡ ይታወሳል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል አመሻሹን በከበባ ላይ ከነበሩት የዝግህ ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል አንዱን አነጋግሯል። በታጣቂዎች ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የተከበቡት አርሶ አደሮችም እስከ ቀኑ 9:30 ሰዓት ተከበው ከቆዩ በኋላ መከላከያ ደርሶ ከርቀት መትረጊዬስ በመተኮስ የመውጫ ክፍት ቦታ እንዲያገኙ በማድረጉ በአደጋ ላይ የነበሩ ወገኖች ሁሉ ያለምንም ጉዳት አምልጠዋል። ያነጋገርናቸው አባት ሲቀጥሉ እንደ ፈጣሪ ፍቃድ ሆኖ ሶስት ጊዜ ከተተኮሰብኝ ጥይት ተርፌያለሁ ብለዋል። በከበባ ቆይተው ከተለቀቁትም አማራዎች፣ኦሮሞ፣ ሽናሻና የሌላ ብሄር ተወላጆች እንዳሉበትም ተወስቷል። ላለፉት 2 ወራት በጥበቃ ስራ ላይ ነው የምናድረው ያሉት የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት በቂ ሀይል መድቦ የህዝቡና ደህንነት እንዲያስከብር፣ በአሸባሪዎች ላይም ቆራጥ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። በተመሳሳይ ዜና ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ሰዓት ጀምሮ የጉምዝ ታጣቂዎች በድባጤ ወረዳ አዘምና ቦኖሽ ቀበሌ ላይም የ6 አባዎራዎችን ቤት ስለማቃጠላቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከከበባ ካመለጡት መካከል ከአንድ አባት ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply