በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በግልገል በለስ መውጫ በኩል የአሸባሪው ትሕነግ ፣ ኦነግ ሸኔ ፣ የወራሪው ሱዳን ተላላኪዎች እና የጉምዝ ታጣቂዎች ተኩስ ከፈቱ። አሻራ ሚዲያ መስከረም 3 ቀን 20…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በግልገል በለስ መውጫ በኩል የአሸባሪው ትሕነግ ፣ ኦነግ ሸኔ ፣ የወራሪው ሱዳን ተላላኪዎች እና የጉምዝ ታጣቂዎች ተኩስ ከፈቱ። አሻራ ሚዲያ መስከረም 3 ቀን 2014 ዓ.ም መስከረም 3 ቀን 2014 ዓ.ም ባህርዳር – ኢትዮጵያ ከመተከል ዞን ድባጤ የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው መስከረም 3 ቀን 2014 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በግልገል በለስ መውጫ በኩል የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎች ተኩስ ከፍተዋል።… እነዚህ ለወራሪው ሱዳን ፣ ለአሸባሪ ፣ ጽንፈኛ ተስፋፊ ትሕነጋዊያንና ኦነጋዊያን በተላላኪነት እያገለገሉ የሚገኙት የጉምዝ ታጣቂዎች የመተከል እና አካባቢው ማህበረሰብ ሰላምና ደህንነት በተደጋጋሚ በማመስ ላይ ናቸው። በተለይ ደግሞ በአማራ ላይ ተደጋጋሚ የጅምላ ፍጅት በመፈፀም መተከልን በደም እያጨቀዩ መሆኑ ግልፅ ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች በድባጤ ከተማ በቅርብ ርቀት በግልገል በለስ መውጫ በኩል የከፈቱትን ጥቃት ለመቀልበስ የአማራ ልዩ ኃይል ፣ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ልዩ ኃይል ፣ የፌደራል ፖሊስ ፣ ሚሊሾችና የአካባቢው ማህበረሰብ በተባበረ ክንድ ተነስቶ እያሳደዳቸው መሆኑንም መረጃዎቻችን ገልፀዋል። አሻራ ሚዲያ – የአይበገሬዎቹ ልሳን!!! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 Telegram :- https://t.me/asharamedia24 Yotube:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply