በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ታጣቂዎች በንፁሃን ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተሰማ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-5/03/2013/ ባህር ዳር ከአርብ ምሽት ጀምሮ በታጣቂዎች የተከፈተው…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ታጣቂዎች በንፁሃን ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተሰማ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-5/03/2013/ ባህር ዳር ከአርብ ምሽት ጀምሮ በታጣቂዎች የተከፈተውን ተኩስ የአካባቢው ነዋሪዎች ሲከላከሉ መቆየታቸውንም ገልጸዋል፡፡ ከምሽቱ ተኩስ በተጨማሪ ኅዳር 5 ጠዋት ከወንብራ ወደ ባሕር ዳር ተሳፋሪዎችን ይዞ በመጓዝ ላይ ያለ ተሽከርካሪ መታገቱንም ነዋሪዎቹን ገልፀዋል፡፡ “በስፍራው ያለው የመከላከያ ኃይል ከታጣቂዎቹ ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ አስቸኳይ እና የተጠናከረ እርምጃ እንዲኖር ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡ ከምሽቱ ተኩስ በተጨማሪ ኅዳር 5 ጠዋት ከወንብራ ወደ ባሕር ዳር ተሳፋሪዎችን ይዞ በመጓዝ ላይ ያለ ተሽከርካሪ መታገቱንም ነዋሪዎቹን ገልፀዋል፡፡”በስፍራው ያለው የመከላከያ ኃይል ከታጣቂዎቹ ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ አስቸኳይ እና የተጠናከረ እርምጃ ያስፈልጋል” እንዲኖር ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡ ከሐሙስ ጀምሮ የሕወሓት ተልዕኮ ያላቸው ቡድኖች በክልሉ ጥቃት ፈፅመዋል ያለው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ዛሬ ኅዳር 5 ደግሞ የወረዳ አስተዳዳሪው ደበሊ ባልጋፎን ጨምሮ የፀጥታ አካላት በታጣቂዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል፡፡ ታጣቂዎቹ ባገቱት ተሽከርካሪ ውስጥ የተሳፈሩ ተሳፋሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውንም የክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ በየነ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም በቂ የሆነ የፀጥታ ኃይል የለም ፤ የሚመለከተው አካል ይህን ተገንዝቦ አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እንዲፈልግ ሲሉ ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply