በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በምግብ፣ በአልባሳት እና በመጠለያ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ተናገሩ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-12/3/13/ዓ.ም ባህር ዳር በቤኒሻንጉል…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በምግብ፣ በአልባሳት እና በመጠለያ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ተናገሩ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-12/3/13/ዓ.ም ባህር ዳር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ሳምቦሰሪ፣ አልባሳን፣ ጋፋሪ፣ ሙዘን፣ ወንበራ ፤ቆርቃ፣ ያምፕ፣ አዲስ ዓለም እና በሌሎችም ቀበሌዎች ንጹኀን አማራዎች ሞትና መፈናቀል ደርሶባቸዋል፡፡ ከሞት የተረፉትና ግድያውን ሸሽተው በድባጤ ወረዳ ጋሊሳ ቀበሌ እና በድባጤ ከተማ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው፤ በምግብ፣ በአልባሳት እና መጠለያ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም መንግስት ይድረስልን ችግር ላይ ነን ሲሉ ዛሬ ህዳር 12/03/2013 መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ ,ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply