በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ከአገር አፍራሽና ነፍሰ ገዳይ ጽንፈኞች የጅምላ ግድያ፣መፈናቀልና ዝርፊያ የተረፉ አማራዎች መንግስት የደረሰ ሰብላቸውን ለመሰብሰብ ምቹ ሁኔታ እን…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ከአገር አፍራሽና ነፍሰ ገዳይ ጽንፈኞች የጅምላ ግድያ፣መፈናቀልና ዝርፊያ የተረፉ አማራዎች መንግስት የደረሰ ሰብላቸውን ለመሰብሰብ ምቹ ሁኔታ እን…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ከአገር አፍራሽና ነፍሰ ገዳይ ጽንፈኞች የጅምላ ግድያ፣መፈናቀልና ዝርፊያ የተረፉ አማራዎች መንግስት የደረሰ ሰብላቸውን ለመሰብሰብ ምቹ ሁኔታ እንዳልፈጠረላቸው ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች በተለይም ከህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ በቂዶህ፣በያምፕ፣ በውብሊሽ፣በገሰስ፣በአልባሳ፣በሙዘን፣በገፈሪ፣ በአንግቶክና በሌሎችም አካባቢዎች በአማራ ላይ ያነጣጠሩ አሰቃቂ ጥቃቶች መፈፀማቸውና በዚህም በርካታ ንፁሀን በግፍ መገደላቸው፣ መቁሰላቸው እንዲሁም በሽህዎች የሚቆጠሩት መፈናቀላቸውና መዘረፋቸው በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል። ተፈናቃዮችም በደረሰባቸው ድርብርብ በደል ከቀያቸው ተሳደው ወደ ጋሌሳ ቀበሌ መጓዛቸውና በግፍ የተገደሉትን ወገኖቻችን አስከሬን አንስተን አፈር ለማልበስ እንዲሁም የደረሰ ሰብላችን እንሰብስብ ዘንድ ኃይል መድቡልን በማለት የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣የዞንና የድባጤ ወረዳ አመራሮችን ከጠየቁ አንድ ሳምንት አልፏል፤ መፍትሄ ሰጭ ግን አልተገኘም። በወቅቱም ታገሱ፣ አሁን ላይ በቂ ሀይል የለንም ከማለት ያለፈ ምላሽ አልሰጡንም ያሉት ተፈናቃዮቹ አንድ ጊዜ ብቻ የተወሰኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ አልባሳ ቀበሌ አቅንተው ከአቅማችን በላይ ነው የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ያወሳሉ። በተለይ ሙዘንን ጨምሮ በተለያዩ ቀበሌዎችም አስከሬን ለማንሳት አለመቻሉን ጠቅሰው ከዚህ ጥቃት በስተጀርባ የመንግስት አካላት፣ኦነግ ሸኔ፣ የጉምዝ ታጣቂዎችና የሕወሓት ፅንፈኞች እጅ እንዳለበት ይታወቃል ብለዋል። ተፈናቃዮቹ አሁን ላይ በቂም ባይሆን የተወሰነ እርዳታ እየመጣላቸው መሆኑን ገልፀው ከፍተኛ የሆነ የመጠለያ ችግር አለብን ብለዋል። መንግስት በጋሌሳ ቀበሌ አዳራሽ ወይም ጊዜያዊ መጠለያ እንኳ ማዘጋጀት ባለመቻሉ አምስት፣ አስር እና ሀያ በመሆን በግለሰብ ቤት ለመጠለል ተገደናል ብለዋል። ተፈናቃዮች እንደሚሉት ከሰሞኑ ኦነግ ሸኔ እንዲሁም የጉምዝ ታጣቂዎችን ያሰማራው የጉህዴን ድርጅት በአልባሳ ቀበሌ አብረው ለመስራት ስምምነት ስለማድረጋቸውና የዘረፉትን የቁም እንሰሳት፣እህልና ሌሎች ንብረቶችንም ወደ ቆርቃ ቀበሌ እያዘዋወሩ ነው ብለዋል። ከአገር አፍራሽና ነፍሰ ገዳይ ጽንፈኞች የጅምላ ግድያ፣መፈናቀልና ዝርፊያ የተረፉ አማራዎች አሁንም መንግስት የመጠለያ ችግራቸውን እንዲፈታላቸውና የደረሰ ሰብላቸውንም ለመሰብሰብ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥርላቸው ጠይቀዋል። የድባጤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደበሌ በልጋፎን ችግሩን ለመፍታት ምን እየተሰራ እንደሆነ ለመጠየቅ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ለጊዜው አልተሳካም። ፎቶ: ፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply