በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የኦነግና ሌሎች ጸረ ሠላም ኃይሎች ንጹሀን የአማራ ተወላጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸው ተገለጸ፡፡                አሻራ ሚዲያ…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የኦነግና ሌሎች ጸረ ሠላም ኃይሎች ንጹሀን የአማራ ተወላጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸው ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የኦነግና ሌሎች ጸረ ሠላም ኃይሎች ንጹሀን የአማራ ተወላጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸው ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-29/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የኦነግና ሌሎች ጸረ ሠላም ኃይሎች ንጹሀን የአማራ ተወላጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ሰሞኑን ከመተከል ዞን የተላኩ ሰዎች ህዝቡን ለማወያየት ወደ ድባጤ ወረዳ ከሆዱ በኋላ ‹‹አሁን ሠላም ነው፤ ሰብላችሁን በሠላም መሰብሰብ ትችላላችሁ›› የሚል መልዕክት እንዳስተላለፉላቸው ገልጸው አርሶ አደሮችም በተነገራቸው መሰርት በጋራ ሆነው ሰብላቸውን መሰብሰብ መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ አርሶ አደሮቹ ሰብላቸውን በሚሰበስቡበት ሰዓት በጫካ ውስጥ የነበሩ አጥፊ ኃይሎች በመክበብ 14 ንጹኃን ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደሏቸው ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ገልጸውልናል፡፡ ጥቃቱን የፈጸሙት ደግሞ የቀበሌና የዞን እንዲሁም የወረዳ አስተዳደር ከኦነግ ታጣቂዎች ጋር በመተባበር እንደሆነም በቦታው የነበሩ ምንጫችን ተናገረዋል ፡፡ በድባጤ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች በአልባሳ፣ ቆርቃ፣ ሙዘን፣ ጋሊሳና በአዋሳኝ የቡለን ወረዳ አጎራባች ቀበሌዎች የኦነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚንቀሳቀሱ ክልሉ የደረሰበት መሆኑን ነዋሪዎች አስረድተዋል፡፡ ሆኖም ግን ጥቃቱን ማስቆም እንዳልተቻለ ነግረውናል፡፡ ስለሆነም የድባጤ ከተማ በሀዘን ድባብ የተዋጠችና አስፈሪ ሁኔታ የሚስተዋልባት በመሆኗ ነዋሪዎች አሁንም በስጋት ውስጥ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ለሚመለከተው አካላት ብናመለክትም ምንም አይነት መልስ ሊሰጡን አልቻሉም ሲሉም ጠቁመዋል፡፡ በመጨረሻም ነዋሪዎቹ የሚመለከተው የመንግስት አካላት ይድረስልን ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply