በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የጨሊያ ቀበሌ ነዋሪዎች መንግስት የኦነግ ሸኔ እና የጉምዝ ታጣቂዎችን የእለት ከእለት እንቅስቃሴ በመገምገም አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳሰቡ። አማራ…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የጨሊያ ቀበሌ ነዋሪዎች መንግስት የኦነግ ሸኔ እና የጉምዝ ታጣቂዎችን የእለት ከእለት እንቅስቃሴ በመገምገም አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳሰቡ። አማራ…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የጨሊያ ቀበሌ ነዋሪዎች መንግስት የኦነግ ሸኔ እና የጉምዝ ታጣቂዎችን የእለት ከእለት እንቅስቃሴ በመገምገም አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጨሊያ ቀበሌ ነዋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው መንግስት በጨሊያ ቀበሌ ያለውን የኦነግ ሸኔ እና የጉምዝ ታጣቂዎችን የእለት ከእለት እንቅስቃሴን በመገምገም ተገቢ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ይጠቁሟል። የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅም ያለአድሎ አገልግሎት የሚሰጡ የፀጥታ አካላትን በማሰማራት በጨፍጫፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ነው የጠየቁት። የኦነግ ሸኔ እና የጉምዝ ታጣቂዎች በአካባቢው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙና ጥቃት እንፈፅማለን በማለት እያስፈራሩ መሆኑን ተገንዝቦ በህዝብ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ነው የጠየቁት። ከቀበሌ እስከ ወረዳ ብሎም ጋሌሳ እስካሉት የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ድረስ መረጃ እንዲደርስ ብናደርግም ትኩረት የሰጡት አልመሰለንም ብለዋል ነዋሪዎቹ። መንግስት የምንሰጠውን መረጃ፣ስጋታችንና የቡድኖችን እንቅስቃሴ እየገመገመ የፀጥታ ስራ ካልሰራ በእያንዳንዱ ቀን ምን ሊከሰት እንደሚችል እርግጠኞች አይደለንም ነው ያሉት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply