You are currently viewing በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጋሌሳ በተባለ ቀበሌ ከብቶችን ሲጠብቁ የነበሩ ሁለት አማራዎች ታገቱ፤ ነዋሪዎች በቀበሌው ያሉ የልዩ ኃይል አባላት ከከተማ እንድንወጣ አልተፈቀደልንም በማለት እያገዙ…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጋሌሳ በተባለ ቀበሌ ከብቶችን ሲጠብቁ የነበሩ ሁለት አማራዎች ታገቱ፤ ነዋሪዎች በቀበሌው ያሉ የልዩ ኃይል አባላት ከከተማ እንድንወጣ አልተፈቀደልንም በማለት እያገዙ…

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጋሌሳ በተባለ ቀበሌ ከብቶችን ሲጠብቁ የነበሩ ሁለት አማራዎች ታገቱ፤ ነዋሪዎች በቀበሌው ያሉ የልዩ ኃይል አባላት ከከተማ እንድንወጣ አልተፈቀደልንም በማለት እያገዙን አይደለም ብለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጋሌሳ በተባለ ቀበሌ ከብቶችን ሲጠብቁ የነበሩ ሁለት አማራዎች መስከረም 2 ቀን 2013 ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ታግተዋል፤ አብረው የነበሩ 3 እረኞች ሮጠው አምልጠዋል። ከእገታው ሮጠው ያመለጡ አባት እንደሚሉት አቶ የሱፍ እና ሌላ አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ ከብቶችን ሲጠብቁ የነበሩ የአማራ አርሶ አደሮች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ታግተዋል። የታጋች ቤተሰብና የአካባቢው ነዋሪዎች ከመስከረም 2 ቀን 2014 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ፍለጋ ላይ ቢሆኑም በአካባቢ ያሉ ልዩ ኃይሎች ከከተማ እንድንወጣ አልተፈቀደልንም በማለት እየተባበሩን አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል። የወረዳው እና የጋሌሳ ቀበሌ ሊቀመናብርት አካባቢው ሰላም ነው በማለት ሀሰተኛ መረጃ በመስጠት የአማራ ልዩ ኃይል እንዳይገባ ግርገራ እያደረጉ ነው ሲሉም ወቅሰዋል። በመሆኑም የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው የጠየቁት ነዋሪዎች በጋሌሳ ቀበሌ ያሉ ተፈናቃዮችም የወገን ድጋፍ በእጅጉ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply