በመተከል የታዙ 17 ታጣቂዎች የአማራ ክልልን ልዩ ሀይል መለዮ የለበሱ እንደሆነ ኮማንድ ፖስቱ ገለፀ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 25፣ 2013ዓ.ም)  ታጣቂዎቹ የተለያዮ ሲምካርዶች፣ መታከሚያ መድሃኒ…

በመተከል የታዙ 17 ታጣቂዎች የአማራ ክልልን ልዩ ሀይል መለዮ የለበሱ እንደሆነ ኮማንድ ፖስቱ ገለፀ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 25፣ 2013ዓ.ም) ታጣቂዎቹ የተለያዮ ሲምካርዶች፣ መታከሚያ መድሃኒ…

በመተከል የታዙ 17 ታጣቂዎች የአማራ ክልልን ልዩ ሀይል መለዮ የለበሱ እንደሆነ ኮማንድ ፖስቱ ገለፀ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 25፣ 2013ዓ.ም) ታጣቂዎቹ የተለያዮ ሲምካርዶች፣ መታከሚያ መድሃኒት እና የአማራ ልዮ ሀይልን የደንብ ልብስ ለብሰው ተገኝተዋል፡፡ ከአማራ ልዩ ሀይል የደንብ ልብስ ባሻገር የቢሻንጉልን ልዮ ሀይል የደንብ ልብስ ለብሰዋል፡፡ ታጣቂ ቡድኖች ከህክምና እስከ ትጥቅ የተደራጁ እና በመንግስት የሚደገፉ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ የኦነግም ትጥቅ እና ስንቅ በመንግስት የሚደገፉ እንደሆነ ከታጠቀው መሳሪያ እና ከያዘው ሎጂስቲክስ መረዳት ተችሏል፡፡ ታጣቂዎቹ የህክምና ቡድን ሁሉ አቋቁመው ንፅሃንን እየገደሉ ሲሆን ፣ከውጭ ሱዳን እና ግብፅ በድጋፍ እንደቆሙ የአሻራ ጭምጭምታ ያሳያል፡፡ የመተከል ኮማንድ ፓስት በግልፅ ጉባ ላይ ያለው እልቂት የህዳሴውን ግድብ መሰረት ያደረገ እንደሆነ አሳውቋል፡፡ ከወለጋ በካማሺ ዞን አድርገው ወደ ድባጤ የሚመጡ ታጣቂዎች ዛሬም በድባጤ ስጋት ፈጥረዋል፡፡ ጥቃቶች የማይቆሙት የመንግስት ድጋፍ ስላላቸው እንደሆነ የአሻራ መረጃ ያሳያል፡፡ የፖለቲካ ሴራው ኢትዮጵያን ማፈራረስ ከህዝብ ደግሞ አማራን ማጥፋት መሰረት ተደርጎ በሴረኞች እየተፈፀመ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply