በመተከል ያለፍርድ ለሁለት ዓመት የቆዮ 614  ወጣቶች ዛሬ በዋስ ተቀዋል፡፡ ( አሻራ ጥር 14፣ 2013 ዓ.ም)     በመተከል ንፁሃን ከመጨፍጨፋቸው ባሻገር ፣ ታስረውም ፍርድ አያገኙም፡፡…

በመተከል ያለፍርድ ለሁለት ዓመት የቆዮ 614 ወጣቶች ዛሬ በዋስ ተቀዋል፡፡ ( አሻራ ጥር 14፣ 2013 ዓ.ም) በመተከል ንፁሃን ከመጨፍጨፋቸው ባሻገር ፣ ታስረውም ፍርድ አያገኙም፡፡…

በመተከል ያለፍርድ ለሁለት ዓመት የቆዮ 614 ወጣቶች ዛሬ በዋስ ተቀዋል፡፡ ( አሻራ ጥር 14፣ 2013 ዓ.ም) በመተከል ንፁሃን ከመጨፍጨፋቸው ባሻገር ፣ ታስረውም ፍርድ አያገኙም፡፡ ተገድለውም በስራዓት አይቀበሩም፡፡ መተከል ግልገል በለስ ከተማ ዛሬም ታጣቂው ቡድን ተኩስ ከፍቶ አምሽቷል፡፡ ሁለት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ሲከሰት ገዳይ ሳይሆን ተገዳይ ይታሰራል፡፡ ታስሮም ፍርድ አያገኝም፡፡ ዛሬ ኢዜአ እንደዘገበው 614 ለሁለት ዓመት ያህል ፍርድቤት ያልቀረቡ ወጣቶች በዋስ ተፈተዋል፡፡ ከ24 እስከ 48 ሰዓት እንደ ሁኔታው የግድ ተጠርጣሪ ፍርድቤት መቅረብ ነበረበት ፡፡ በመተከል ለ700 ቀናት ያለምንም ፍርድ የቆዮ ዜጎች ብዙ ናቸው፡፡ የመተከል ዋነኛ ችግር ታጣቂው አይደለም፡፡ ከታጣቂው ጀርባ የመሸገው መንግስታዊ መዋቅር ነው፡፡ ይህ መዋቅር ታጣቂውን በመረጃ በስንቅ፣ በትጥቅ እና በመረጃ ብሎም በስልጠና ይረዳል፡፡ ንፁሃን ዘር ተለይተው እንዲገደሉ ትጥቅ እንዳይታጠቁ ይደረጋል፡፡ ዱላ እንኳን ይዞ የተገኘ ይታሰራል፡፡ ከታሰረ በኃላም ለሁለት ዓመት ያህል ፍርድቤት አይቀርብም፡፡ በመተከል ያለው ችግር መንግስታዊ እና ስራዓት ወለድ ነው፡፡ ጭፍጨፋው ማንነታዊ ነው፡፡ ከታጣቂው ወገን ኦነግ ይሳተፋል፡፡ በቢሻንጉል ነፃነት ግንባር ስር ሱዳንም አለች፡፡ ይሄን ሁሉ ግን በቸልተኝነት ፀጥ ያለ የመንግስት አካል አለ፡፡ የጅምላ ጭፍጨፋው ዛሬም አልቆመም፡፡ መፈናቀሉም ቀጥሏል፡፡ ገዳዮች ዛሬም የመግደል ስልጣን አላቸው፡፡ መንግስት የሽንገላ መግለጫ እየሰጠ ሊቀጥል ፈልጓል፡፡ ምክርቤቱ ለመንግስት የውሳኔ ሀሳብ በመተከል ጉዳይ የሰጠ ቢሆንም፣ አስፈፃሚው አካል አሁንም ቸልተኝነት እያሳየ እንደሆነ የመተከል ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply