በመተከል ዳንጉር ማንቡክ የጉምዝ ልዩሀይል በመከላከያ ትጥቃቸውን ፈተው ከካምፕ እንዳይንቀሳቀሱ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ…

በመተከል ዳንጉር ማንቡክ የጉምዝ ልዩሀይል በመከላከያ ትጥቃቸውን ፈተው ከካምፕ እንዳይንቀሳቀሱ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ…

በመተከል ዳንጉር ማንቡክ የጉምዝ ልዩሀይል በመከላከያ ትጥቃቸውን ፈተው ከካምፕ እንዳይንቀሳቀሱ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዳንጉር ወረዳ በነ ደርጉ እና ገብረመድን በተባሉ ባለሀብቶች የሚደገፉ ቁጥር(3 ላይ) ከትናንት ከቀኑ 9:00ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና በህውሓት የሚመራው ጉምዝ ጋር ውጊያ እንደገጠሙ መግለፃችን ይታወሳል። የውጊያው መንስኤም በክልሉ ልዩሀይል ታጅበው ከጉብላክ ወደ ማንቡክ በመጓዝ ላይ በነበሩ ተጓዦች ላይ ተኩስ በመክፈት እና ተሽከርካሪውን በማስቆም 12 ሴት ነርሶችን በማገታቸው ነው ሲል የመተከል ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ገልፆልናል። ይሄን የሰማው የመከላከያ ሰራዊት የታገቱ 12 ሴት ነርሶችን ለማስለቀቅ ሞክሮ አልተሳካለትም በዚህ የተኩስ ልውውጥ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ልዩሀይል መከላከያ ሰራዊቱን በመክዳት ከአጋች ቡድኑ ጎን በመሆን ስድስት(6)የመከላከያ ሰራዊት አባላት ገድለዋል። በዛሬው እለትም ቁጥራቸው ያልታወቀ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሞተዋል። መከላከያ ሰራዊቱም በዛሬው እለት በወሰደው የአፀፋ እርምጃ 16 የአጋች ቡድን አባላትን መግደል ችሏል። በዓሁኑ ሰዓትም የመከላከያ ሰራዊቱ በአካባቢው ያለውን የክልሉን ልዩ ሀይል ትጥቅ በማስፈታት ከካምፕ እንዳይንቀሳቀሱ አድርጓል። ይሁን እንጂ መከላከያ ሰራዊቱ እንደፈለገ ተንቀሳቅሶ አጋቾችን ለመደምሰስ እየተቸገረ እንደሆነም የመረጃ ምንጫችን የገለፁልን ሲሆን ህብረተሰቡ ከመከላከያ ጎን ለመሰለፍ ቢሞክርም በክልሉ በንግስት ይሁንታን አላገኘም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከታገቱ 12 ሴት ነርሶች መካከል 7ቱ ሲለቀቁ 5ቱ አንድ ወንድ እና 4 ሴቶች አሁንም አልተለቀቁም። ዘገባው የአሻራ ሚዲያ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply