በመተከል ድባጤ ወረዳ የጉምዝ ታጣቂዎች በቂዶህ ቀበሌ በፈፀሙት ጥቃት 12 አማራዎች ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ  የአ…

በመተከል ድባጤ ወረዳ የጉምዝ ታጣቂዎች በቂዶህ ቀበሌ በፈፀሙት ጥቃት 12 አማራዎች ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአ…

በመተከል ድባጤ ወረዳ የጉምዝ ታጣቂዎች በቂዶህ ቀበሌ በፈፀሙት ጥቃት 12 አማራዎች ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ምንጮች ከድባጤ ወረዳ እንደገለፁት ህዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም የጉምዝ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት 12 አማራዎች በእርሻ ማሳቸው ላይ እያሉ ተገድለዋል። ይኸውም ህዳር 27 ቀን 3 ፣ ትናንት ህዳር 28 ቀን ደግሞ 9 አስከሬን በቂዶህ መገኘቱንና ስርዓተ ቀብራቸውም መፈፀሙን አስታውቀዋል። የመከላከያ ሰራዊትና ልዩ ሀይሉ ታጣቂዎች ጥቃት በፈፀሙባቸው በቡለን፣ በድባጤ በጉልፈንና በኮመድ ቀበሌዎች የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዛሬው እለትም በኮመድ ቀበሌ ከማለዳው 3 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6 ሰዓት የጉምዝ ታጣቂዎች ተኩስ በመክፈታቸው የአካባቢው ሚሊሻና የፀጥታ መዋቅሩ በጋራ የአፀፋ ምላሽ መስጠቱንና የተጎዳውን በተመለከተ መረጃው የለንም ብለዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በጉልፈን፣በሳስማንደድና በፋርዘይት ቀበሌዎች እንዲሁም በቡለን ጭላንቆ ቀበሌ ላይ ስጋት በመኖሩ በማህበረሰቡና በፀጥታ አካሉ በኩል አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ነው ነዋሪዎች ያሳሰቡት። የቤንሻንጉል ጉምዝ ልዩ ሀይል በትናንትናው እለት ከተለያዩ የድባጤ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በጋሌሳ ካሉ አማራዎች የተወሰኑትን በመሰብሰብ ታረቁ ማለታቸውንና ነገር ግን ከእርቅ በፊት አስከሬን ይነሳ፣ነፍሰ ገዳዮች በህግ ይጠየቁ፣የተዘረፈው ንብረት ይመለስ፣ሰብላችን ይሰብሰብ የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸው ተገልጧል። ለማግባባት በሚል ስምም ከተፈናቃዮች 4 የሚሆኑትን አስገድደው በመውሰድ ስብሰባ ቢቀመጡም የአልባሳ የጉምዝ ታጣቂ ተባባሪዎች አንመጣም በማለታቸው ውይይቱ አልተሳካም ተብሏል። ዛሬ ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም በተመሳሳይ ከክልል የመጡ አመራሮችና የፀጥታ ኃላፊዎች መከላከያ ቢመጣ እንዴት ትደግፉታላችሁ በማለት የጋሌሳ ቀበሌ ነዋሪዎችን መጠየቃቸውን ተከትሎ ወደ አካባቢው ገብቶ ሰላምና ደህንነታችን ያስፍንልን እንጅ ለመተባበር ዝግጁ ነን በማለት ቃል ስለመግባታቸው ተናግረዋል። ነዋሪዎች ከጉምዝ ታጣቂዎችና ከኦነግ ሸኔ አባላት ጋር መረጃ በመለዋወጥ፣ንፁሀንን በማስገደል፣ በመዝረፍና በማፈናቀል የተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ ስለምን አትወስዱም ሲሉ ጠይቀዋል። በውይይቱ ላይ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው እንዴት እንመልስ፣ አስከሬን እንዴት ይነሳ፣ለሰብአዊ እርዳታው ከማን ምን ይጠበቃል፣የደረሰ ሰብላቸው እንዴት እንሰብስብና የመሳሰሉ ጉዳዮች አለመነሳታቸው እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል። በተመሳሳይ በድባጤ በአንግቶክ ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎች ከውስጥ ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን የተፈናቀሉ አማራዎችን የደረሰ ሰብል ለራሳቸው እየሰበሰቡ መሆኑ ተጠቁሟል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply