You are currently viewing በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች  ከሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ እየለቀቁ በመውጣት ላይ መሆናቸው ተገለጸ፤ አንዳች መንግስታዊ ዋስትና የለንም፤ ውሃ እንኳ ወጥተን ለመቅዳት አልቻልንም ሲሉ…

በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ከሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ እየለቀቁ በመውጣት ላይ መሆናቸው ተገለጸ፤ አንዳች መንግስታዊ ዋስትና የለንም፤ ውሃ እንኳ ወጥተን ለመቅዳት አልቻልንም ሲሉ…

በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ከሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ እየለቀቁ በመውጣት ላይ መሆናቸው ተገለጸ፤ አንዳች መንግስታዊ ዋስትና የለንም፤ ውሃ እንኳ ወጥተን ለመቅዳት አልቻልንም ሲሉ አማረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ከሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ እየለቀቁ በመውጣት ላይ ስለመሆናቸው ገልጸዋል። በተደጋጋሚ ላቀረብናቸው ጥያቄዎች አንዳች መንግስታዊ ምላሽ እና ዋስትና አላገኘንም የሚሉት ነዋሪዎች ውሃ እንኳ ወጥተን ለመቅዳት አልቻልንም ሲሉ አማረዋል። ከአቢ ደንጎሮ ወረዳ በተለይ ከቱሉዋዩ ቀበሌ እየተፈናቀሉ ወደ ቱሉጋና እና አንገር ጉትን እየተሰደዱ መሆኑ ተገልጧል። በተለያዩ ጊዜያት መንግስት በአስቸኳይ የፌደራል የጸጥታ አካላትን እንዲመድብላቸው ቢጠይቁም አንድም ምላሽ የሚሰጥ አካል አልተገኘም ይላሉ። በአካባቢው የሚኖሩ አማራዎች በወረዳውና በሆሮ ጉድሩ ዞን የመስተዳድር አካላት ፍጹም አመኔታ ስለማጣታቸው ከንግግራቸው ለመረዳት ተችሏል። አሸባሪው ኦነግ ሸኔም ከመስተዳድር አካላት ጋር በመመሳጠር በአማራ ላይ የለየለት የዘር ፍጅት እየፈጸመ መሆኑ ግልጽ ነው። መንገድ ከተዘጋም ወራት በመቆጠሩ ከፍተኛ የሆነ ርሃብ መኖሩ እየተነገረ ነው። ቱሉጋና እና አንገር ጉትንም ከአቅማቸው በላይ ብዙ ሽህ የአማራ ተፈናቃዮችን እየተቀበሉ በመሆኑ በሁለንተናዊ ምስቅልቅል ውስጥ ይገኛሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply