በመቶዎች የሚቆጠሩ የዋግነር ተዋጊዎች በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ከሩሲያው የደህንነት ተቋም ዋግነር ጋር የተገናኘ የመልእክት መላላኪያ መተግበሪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎቹ ወደ መካከለኛው አፍሪቃ ሪፐብሊክ (ሲአር) መድረሳቸውን ትላንት እሁድ እለት ተናግሯል።

ከ2018 ጀምሮ ቢያንስ አንድ ሺህ የሚሆኑ ቅጥረኞች በሀገሪቱ ወስጥ ይገኛሉ፡፡

የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች ወደ 600 የሚጠጉ ቅጥረኞች ሩሲያን ለቀው መውጣታቸውን ይናገራሉ።

ከዋግነር ቡድን ጋር የተገናኘ ኩባንያ እንዳስታወቀው አዲሶቹ ቅጥረኛ ተዋጊዎች በዚህ ወር መጨረሻ በ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ውስጥ በሚደረገው ህዝበ ውሳኔ ደህንነትን ለመጠበቅ ይረዳሉ ብሏል ፡፡

ይህም ፕሬዝዳንት ፋውስቲን-አርቼንጅ ቱዋዴራ ለሶስተኛ ጊዜ የስልጣን ዘመን መወዳደር መቻል ፤ አለመቻላቸውን ይወስናል ሲል ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል።

በያይኔአበባ ሻምበል

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply