በመንገድ ስራዎች ላይ የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ዲኤም ሲ (DMC) ወደ ሪል እስቴቱ ዘርፍ መምጣቱን አሳውቋል፡፡

ይህ የኮንስትራክሽን ድርጅት ለቤቶቹ ግንባታ አዲስ የደንበኞችን መጉላላት የሚያስቀር በጥናት ላይ የተመሰረ ቴክኖሎጂ እንደተጠቀመም ገልጿል
በዳረገው ጥናት ቤቶቹ ለደንበኞች ከተሰጡ በኋላ የማማረር ሁኔታ እንዳለ በማንሳት ይህንን ችግር ለቅረፍ ወደስራ እንደገባ ነው ያስታወቀው።

ዲኤም ሲ በለቡ መብራት ሀይል 65 ሺህ 950 ካሬ ላይ ያረፈ ሪል እስቴት ሲሆን የቤቶች ግንባታ የሚወስደውን ጊዜ የሚያሳጥር ሂደቶችን እንደተጠቀመም ተነስቷል
ከ56.6 ካሬዎች ጀምሮ የቤቶችን ግንባታ እያደረገ እንዳለ ያነሳው ዲኤምሲ ዝቅተኛው የቤት ሽያጭ ዋጋውም ከ4 ሚሊየን ብር ጀምሮ እንደሆነም ገልፀዋል።

የውጭ ምንዛሬ የዘርፉ ችግር እንደሆነ ቢነሳም የሀገር ውስጥ ምርትን በመጠቀም ችግሩን ለመቅረፍ ዲኤምሲ ሪል እስቴት እየሰራ እንደሆነም ተነስቷል
በታምኝነታችን ምክንያት የዘርፉን ውድድር በመምራት ላይ እንደሚገኝ ሲገለፅ:

በየብሎኩ ከ200 በላይ አባውሮችን እንደሚይዝ እና በብር ደረጃም ከአንድ ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የቤት ቅናሽ እንዳደረጉም ተገልጿል።

በውጭ እና በሀገር ውስጥ ባሉ የሪል እስቴት ባለሞያዎች አስገምግመው ወደስራ እንደገቡ ሲገለፅ በተለይም በመንገድ ስራው ላይ ያላቸውን የረጅም ጊዜ ልምድ በመጠቀም ጥሩ ስራ እየሰሩ እንዳሉ ጠቁመዋል።

ከ56.6 ካሬዎች ጀምሮ የቤቶችን ግንባታ እያደረገ እንዳለ ያነሳው ዲኤምሲ ዝቅተኛው የቤት ሽያጭ ዋጋውምከ4 ሚሊየን ጀምሮ እንደሆነም ገልፀዋል።
ሪል እስቴቱ አንድ ቤት ለሚገዛ ተጨማሪ የቤት ስጦታ እጣ ውስጥ እንደሚካተትም ተነስቷል፡፡

ለዘርፉ አልሚዎች ችግር የነበረውን ግብአቶችን የማግኘት ችግርን ዲኤምሲ እራሳቸው በማምረት ችግሩን በመቅረፍ ጥሩ መንገድ ላይ እንደሆኑም አንስተዋል።

ከ2 አስርት አመታት በላይ በዘርፉ ልምድ እንዳለው የሚነገረው ዲኤምሲ ከዚህ ቀደም የሀዋሳ የአርባምንጭ የመሳሰሉትን መንገዶችን ከለምንም ሁለተኛ ጥገና በስራ ላይ እንዳዋለም ተገልጿል፡፡

በለዓለም አሰፋ

መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply