በመንግሥት ውስጥ መንግሥት! በኢትዮጵያ ውስጥ ኦሮሚያ! ወይስ በኦሮሚያ ውስጥ ኢትዮጵያ! ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

ሌንጮ ለታ፣ ሌንጮ ባቲ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ግርማ ብሩ፣አብይ አህመድ፣ አባዱላ ገመዳ፣ታዬ ደንደአ፣አዲሱ አረጋ የሻሸመኔ፣ የመተከል፣ የወለጋ፣ የሰሜን ሸዋ  የአማራ አራጆች ለፍርድ ይቅረቡ!!!  እነዚህ አዲሶቹ የኦሮሚያ ሹማምንቶች በኢትዮጵያን ሃገረ መንግሥት በአንድ በኩል በህጋዊነት እየገዙ በሌላ በኩል በህገወጥነት ውስጥ ውስጡን በመንግስት ውስጥ ስውር መንግሥት በማቌቌም ህጋዊ ያልሆነ የግንኙነት መረብ በመዘርጋት በዘር ላይ የተመሠረተ አደረጃጀት፣ አንድ ለአምስት በማደራጀት የኦነግን ኦሮሙማ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ፍኖተ-ካርታ ዘርግተው በመዝረፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኦሮሚያ ከልልን በሁሉም አቅጣጫ በማስፋፋት አዲሱን የኦሮሙማ ካርታ ከትግራይ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ሀረሪ፣ ድሬዳዋ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እስከ ኬንያ የሚዘልቅ መሆኑን ካርታውን ከላይ ማየት ይቻላል፡፡ “Deep State:-A deep state is a type of governance made up of potentially secret and unauthorised networks of power operating independently of a state’s political leadership in pursuit of their own agenda and goals.” Wikipedia የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) የኦሮሞ ህዝብን በስብዓዊ ጋሻነት አፍኖ በመያዝ ሰው በማረድ፣ ህፃናት በመግደል፣ ሴት በመድፈር፣ ህዝብ በማፈናቀል ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ፈፅመዋል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ የኦነግ ማፍያ ቡድን ሊታገለው ይገባል እንላለን፡፡

 

ሻብያ፣ ወያኔና ኦነግ አንድም ሦስትም ናቸው!!! ኢትዮጵያን ለዘመናት ለማፍረስ በጋራ የነደፉት የትግል ስልት  አንኳሮቹ ውስጥ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ኤርትራን፣ ትግራይን ኦሮሞን ደቡብ ኢትዮጵያን፣ ሱማሌን፣ አፋርን፣ ቤኒሻንጉልን፣ ጋምቤላን፣ ወዘተ በቅኝ ግዛትነት ገዝታለች ስለዚህ ነው በፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል ያደረግነው ይላሉ፡፡ በዚህም መሠረት በዘር ላይ የተመሠረተ ነፃ አውጪ ድርጅቶች በመመሥረት በሃገሪቱ የጦር አበጋዞች መንግሥት የተፈለፈሉት፡፡ የጦር አበጋዞቹ ድንበር የማስፋፋት ፖሊሲ ስትራቴጂና ታክቲክ ሃገሪቱን ወደማያባራ ጦርነት ውስጥ ከቷል እንላለን፡፡ አቶ አያሌው መንገሻ የቀድሞው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የደህንነት ሹም የነበሩ (ቪዲዬውን ይመልከቱት) ከህብር ራዴዬ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ  የተገኘ መረጃ መሠረት፡- ከመጋቢት ሃያ አራት 2010 እስከ 2013ዓ/ም  ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ መሪ የዶክተር አብይ አህመድ አገዛዝ ዘመን ምድሪቶ በደም ታጠበች፣ በህይወት የመኖር መብት ጠፋ ጣረ-ሞት በኢትዮጵያ እንዳንጃበበ ይገኛል፡፡

 • ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ካማሽ፣ መተከልና አሶሳ ዞኖች ውስጥ ከ2010 እስከ 2013 ዓ/ም ውስጥ 750 ሰዎች ስጋቸው ተበልቶል ደማቸው ተጠጥቶል፣ 265405 የአማራ ህዝብ ብዛት የነበረ ሲሆን በሦስት አመታት ውስጥ 221347  አማራዎች ተፈናቅለዋል፣ 2581 ተገድለዋል፣ 905 የቆሰሉ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ 40572 አማራዎች በክልሉ ውስጥ ይኖራሉ፡፡
 • በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ወለጋ፣ አርሲ ዞን፣ባሌ፣ ኢሉባቡር፣ ጅማ፣ ዝዋይ ኢተያ ውስጥ ከ2010 እስከ 2013 ዓ/ም 2465 ሰዎች ተገድለዋል፣ 1905 ሰዎች ቆስለዋል፣ 839645 ሰዎች ተፈናቅለዋል
 • በደቡብ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ከ2010 እስከ 2013 ዓ/ም 641 ሰዎች ተገድለዋል፣ 209 ሰዎች ቆስለዋል፣ 105000ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ (1)
 • በትግራይ ክልላዊ መንግስት 52000 ሰዎች ተገድለዋል፣ ሦስት ሽህ ሃያ አራት ህፃናት ወላጆቻቸው እንደጠፉባቸው እንዲሁም ስምንት መቶ ሴቶች ተደፍረዋል፣ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ በትግራየይ የገጠር ከተማዎች ነዋሪዎች መሠረታዊ አቅርቦቶች እንደማይደርሳቸው ዩኒሲኤፍ ሪፖርት አድርጎል፡፡

በ2008 እና 2009ዓ/ም በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞና እንቢተኛነት ምክንያት ከ200 በላይ በሚሆኑ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የቡና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ ከ348 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኢንቨስትመንት ውድመት መከሰቱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዳይሬክተር የፕሮጀክቶች ድጋፍና ክትትል በጥናት በማስረጃ አቅርቦል፡፡ በዚህም የተነሳ በአጠቃላይ ክልሎች ለደረሱ የኢንቨስትመንት ውድመቶች መንግሥት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የማገገሚያ ክፍያ ከፍሎል፡፡ ተጎጂ ድርጅቶች ከሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የተለያዩ እቃዎችን ከቀረጥ ነጻ በሆነ መንገድ እንዲያስገቡ ስለሚደረግ ሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እንድታጣ ያደርጋታል፡፡ የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር የትየለሌ ሆኖ፣ ፋብሪካዎችን፣ እርሻዎች፣ የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች ወዘተ ኢንቨስትመንቶችን እንዳያወድሙ አስፈላጊው ትምህርት ባለማስረፁ ንብረት ማውደም ባህል የሚያገረሽ ዋነኛ ምክንያት ሆኖል፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለሻሸመኔ፣ለአጣዬ፣ ለሸዋ ሮቢት፣ ካራ ቆሬ ከተሞች ኃብትና ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖችና ኢንቨስተሮች በፍጥነት ካሳ ሊሰጥ ይገባል እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ  ወድቃ ትገኛለች በሃገሪቱ  በኮማንድ ፖስት በትግራይ፣  በቢኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ክልል ወዘተ የአስቸኮይ ጊዜ አዋጅ ሥር በኮነሬል አብይ አህመድ ወታደራዊ አገዛዝ  ቀንበር ተጠምዳ ትገኛለች፡፡ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ተሸመድምዶል፣ የሸቀጣ ሸቀጥ የዋጋ ንረት፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረት፣ የብድርና የእዳ ጫና፣ የውጪ ንግድ ገቢ መቀነስ፣ የአውሮፓና አሜሪካ አገሮች እርዳታና ብድር እቀባ  ወዘተ አገሪቱን በኦነግ የፈንጂ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ከቶታል፡፡ Ethiopia under OLF & Command Post Minefield!

የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) በግማሽ ክፍለ ዘመን ትግሉ አንድ መንደር ነፃ አላወጣም:: ለኦዴፓ ብልፅግና የኢትዮጵያ ህዝብ በህዝባዊ እንቢተኛነትና በሰላማዊ ትግል፣ ህዝባዊ ጥያቄ ያቀርባል፡፡

 • በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣የፖሊስ ኃይል፣ ልዩ ኃይል በሻሸመኔ፣ አጣየ ሃምሳ አማራዎች ተገድለዋል፣፣ ወዘተ ህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ በተመሳሳይ
 • በሃገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ የውስጥ ተፈናቃዬች አስቸኮይ የስብዓዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው
 • የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ማድረግ ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ ከሱዳን ዳርፉር ያለው አራት ሽህ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ኃይል ሃር ቤት ገብቶ በትግራይ፣ ወለጋ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሸዋ ወዘተ ገብቶ ሠላም እንዲያስከብር ማድረግ፡፡
 • የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኦነግ ለተቃጠሉት ከተሞች፣ ሻሸመኔ፣ጅማ፣አርሲ፣አጣየ፣ ሸዋ ሮቢ፣ ካራ ቆሬ፣ወዘተ ኃብትና ንብረታቸው ለወደመባቸው አስፈላጊው ካሣ እንዲከፈላቸው፡፡
 • ካማንድ ፖስት ኦሮሚያ ውስጥ ላሉ ኦነግ ሽፍታ እንጅ ላልታጠቁ የአማራ ሰላማዊና ንፅህ ዜጎች ላይ መሆን የለበትም፣ ካማንድ ፖስቱ ከሰሜን ሸዋ ይውጣ!!!
 • የአማራ ክልላዊ መንግሥት አዴፓ ብልጽግና ፓርቲን የምርጫ ድምፅ ካርድ በመንፈግና ባለመምረጥ ከስልጣን እንዲወርዱ ማድረግ ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎን በመምረጥ በምርጫው መሳተፍ ያሻል፡፡

 

{ሀ} ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ  የኦሮሞ ቢሊዮነሮችን ፈጠራ ፕሮጀክቶች…ቢሊዮነር ፍለጋ!!! እውቀትን ፍለጋ!

‹‹ኦሮሞ ፈርስት›› ኦሮሞ ይቅደም!!! ሁሉም ነገር የኦሮሞ ነው፣ የኦሮሙማ በኬኛ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያውን በኦነግ ሠራዊት፣ በጦር መሣሪያና፣ በፀጥታና ደህንነት መረጃ ባንኩን፣ ታንኩን፣ መሬቱን ወርቁን ኃብት አሰባስቦ የኦሮሞ የክልልና የፌዴራል መንግሥትን ለመቆጣጠር የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ ነድፈዋል፡፡ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ  የኦሮሞ ቢሊዮነሮችን ፈጠራ ፕሮጀክቶች ውስጥ የዘረኛና የተረኛነት ስሜት  ከመጋቢት 2010 እስከ 2013ዓ/ም  ለአብነት ያህል፡- የኦሮሞ ሚሊየነር ኃብታሞች ድንቁ ደያስ(የሶደሬ ሪዞርትና ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የሃገር ገንዘብ ዘርፎ አሜሪካ የኮበለለ)፣ አለማየሁ  ከተማ (ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በእራሱ ያደረገ ሙሰኛ በደረቅ ቼክ ወንጀል ተከሶ ኡጋንዳ ኮብልሎ የነበረና በምህረት ዶክተር አብይ ወደ ሃገር የመለሱት  በልጁ ስም አራት መቶ ሚሊየን ብር በብድር የወሰደ)፣ አቶ ገምሹ በየነ የኢሊሊ ሆሌል ባለቤት በዝርፍያና ሙሰኛነት ኮብልሎ የነበረና በምህረት የተመለሰ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ኦሮሙማ የሃገሪቱን የኢኮኖሚ ዘርፍ በመቆጣጠር ላይ ይገኛል ለአብነት ያህል የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች በአመዛኙ ለኦሮሞ ኮንትራክተሮች በዘረኛና ተረኛ ስሜት በመታደል ላይ ይገኛሉ፡-

 

በስድስት ወራት ከ43 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች ውል ተፈረመ፡፡

ከኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት ውስጥ ከፍተኛውን በመውሰድ ከሚጠቀሱት የመንገድ ልማት ዘርፍ አንዱ ነው፡፡ በ2013 በጀት ዓመትም በፌዴራል ደረጃ ለሚገነቡ መንገዶች ከ56 ቢሊዮን ብር በላይ የተመደበ ሲሆን፣ በዓመቱ ውስጥ 117 የመንገድ ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል፡፡…

21 መንገዶች ለመገንባት በጨረታ አሸናፊ ሆነው ሥራውን የተረከቡት የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ቲክስ ኮንስትራክሽን፣ ፉል ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ፣ ኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን፣ ዱጉሳን አንሳት ቲክ – ራባህ ኤንድ ሰንስ፣ ዓለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ፣ ኤኞ ዋልጂ ኮንስትራክሽን፣ ራማ ኮንስትራክሽን፣ ዮቴክ ኮንስትራክሽን፣ ሳናን ኮንስትራክሽን፣ ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን፣ አሰር ኮንስትራክሽን፣ እንይ ኮንስትራክሽንና ዮናብ ኮንስትራክሽን ናቸው፡፡ ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ በዘረኛና ተረኛ ስሜት የመንገድ ኮንስትራክሽን ሥራዎችን ለነቀዙ የኦሮሞ ባለኃብቶች በመስጠት በሙስና ሥርዓቱ ተጨማልቆል፡፡     (2)

 • ዓለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ (አገር በቀል) እና ኤምሲጂኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግል/ማ. የመንገድ ፕሮጀክት ተቋራጭ ነጌሌ ቦረና ዶሎኦዶ መልካሱፍቱ ሎት 1፣ ነገሌ ቦረና ኪ.ሜ 64+500 የመንገድ ግንባታ ሥራ5 ኪሎ ሜትር መንገድ በ1.37 (አንድ ቢሊዮን ሦስት መቶ ሰባ ሚሊዮን) ብር ሥራ ተሠጥቶታል፡፡
 • ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን የመንገድ ፕሮጀክት ተቋራጭ (ነቀምት ሶጌ ካማሽ ቆንቾ ኮንትራት 1 ኪሎ ሜትር 0+000 ኪ.ሜ 104-800 የመንገድ ግንባታ ሥራ ፕሮጀክት) 104.8 ኪሎ ሜትር መንገድ በ35 ቢሊዮን ብር እንዲሁም (ነቀምት ሶጌ ካማሽ ቆንቾ ኮንትራት 2፣ ኪ.ሜ 104+800 ኪ.ሜ 160+000 የመንገድ ግንባታ ሥራ ፕሮጀክት) 55.2 ኪሎ ሜትር መንገድ በ1.92 (አንድ ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ሚሊዮን)  ብር በጠቅላላው 4.27 (አራት ቢሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሚሊዮን) ብር ሥራ ተሠጥቶታል፡፡
 • የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የመንገድ ፕሮጀክት ተቋራጭ የጉደር ከተማ አምቦ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ5 ኪሎ ሜትር መንገድ በ1.03 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ጫንቃ ጊዳሜ ዲዛይንና ግንባታ 97 ኪሎ ሜትር መንገድ በ3.20 (ሦስት ቢሊዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን) ብር በጠቅላላው 4.23 (አራት ቢሊዮን ሁለት መቶ ሠላሳ  ሚሊዮን)ብር ሥራ ተሠጥቶታል፡፡
 • በአጠቃላይ ለኦሮሚያ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ተቋራጮች 87 (ዘጠኝ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሰባ  ሚሊዮን) ብር ሥራ ተሠጥቶታል፡፡ የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮች የተረከቧቸው የመንገድ ግንባታዎች አጠቃላይ ወጪም 27.3 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ የኦሮሞ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ተቋራጮች 36 በመቶ የሥራና የገንዘብ ድርሻ ተቀራምተዋል፡፡
 • በውጭ ዓለም አቀፍ የሥራ ተቋራጭ ድርጅቶች የሚገነቡት83 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸውን መንገዶች ደግሞ 15.9 (አስራአምስት ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሚሊዮን) ብር ዋጋ ያላቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ በ2013 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከተፈረሙት 21 የመንገድ ፕሮጀክቶች የ20ዎቹ የግንባታ ወጪ የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግሥት ነው፡፡ የአንዱ ፕሮጀክት ደግሞ በጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድዖ ድርጅት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግሥት በተያዘ በጀት የሚከናወን ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡…

 

{ለ} መንግሥት በሥሩ ያሉትን አሥር ስኳር ፋብሪካዎች በመሸጥ ገቢው ለዕዳ ክፍያ እንዲውል ተወሰነ

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ

የመንግሥት 13 ስኳር ፋብሪካዎች አሥሩ ለግል ባለሀብቶች ተሸጠው፣ ከሽያጩ የሚገኘው ገቢ በከፍተኛ የዕዳ አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው ተብለው ለተለዩ ሰባት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዕዳ ክፍያ ጥቅም ላይ እንዲውል ተወሰነ።

በመንግሥት የተለዩት ሰባቱ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና፣  አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ኢትዮ ኢንጅነሪግ ግሩፕ (የቀድሞው ሜቴክ)፣ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽንና ስኳር ኮርፖሬሽን ናቸው። ድርጅቶቹ ከአገር ውስጥ አበዳሪዎች በዋናነት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ከውጭ አበዳሪዎች ተበድረው ያልመለሱት አጠቃላይ ዕዳ 780 (ሰባት መቶ ሰማንያ) ቢሊዮን ብር ወይም 19.5 (አስራዘጠኝ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ዶላር ነው፡አዲስ የሚቋቋመው ኮርፖሬሽን ሰባቱ ድርጅቶች ካለባቸው 780 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 570 (አምስት መቶ ሰባ) ቢሊዮን ብሩን ወርሶ የመክፈልና የማስተዳደር ኃላፊነት ተጥሎበታል።

ኮርፖሬሾኑ  የሚያስፈልገው የመጀመርያ ካፒታልም ከመንግሥት በጀት ውጪ እንደሚሆን መረጃው ያመለክታል።

በመሆኑም አሥር የመንግሥት ስኳር ፋብሪካዎችን በመሸጥ የሚገኘው ገቢ የመጀመርያ ካፒታል ፈሰስ እንዲደረግ የተወሰነ ሲሆን፣ ከስኳር ፋብሪካዎቹ ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ በተጨማሪ በቅርቡ ለውጭ ኩባንያዎች ከሚሰጠው የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ክፍያ፣ እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ከፊል ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ትልቅ ድርሻ ወደ ኮርፖሬሽኑ ፈሰስ እንዲደረግ መወሰኑ ታውቋል።

የሀብትና ንብረት ግመታ  ቡከር ቴት የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ተቀጥሮ የግመታ ሥራውን  አጠናቆል፣

ኩባንያው የግመታ ሥራ የ13 ስኳር ፋብሪካዎችን  ሀብትና ንብረት ከዓመት በፊት በነበረ ዋጋ መሠረት 88 (ሰማንያ ስምንት) ቢሊዮን ብር ገምቷል።

የስኳር ፋብሪካዎቹ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ ወለድን ሳይጨምር ብቻውን 81.6 (ሰማንያ አንድ ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ተመሳሳይ ወቅት የፋብሪካዎቹ አጠቃላይ የውጭ ዕዳ መጠን ወለድን ሳይጨምር 2.1 (ሁለት ነጥብ አንድ) ቢሊዮን ዶላር ነበር።

የ13 ስኳር ፋብሪካዎች አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ዕዳ ወለድን ሳይጨምር፣ በአሁኑ ወቅት ባለው የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥሌት 165.6 ቢሊዮን ብር ይሆናል። ይሁን እንጂ ይህ ግመታ ከተከናወነ በኋላ መንግሥት ተጨማሪ ወጪዎች በስኳር ፋብሪካዎች ላይ በማፍሰሱ የምርት ማሻሻያ ሥራዎችን፣ እንዲሁም የተመረጡ ፋብሪካዎችን የግንባታ ደረጃ የማሻሻል ጥረቶችን ያደረገ በመሆኑ፣ በቀደመው የሀብት መጠን ላይ ለውጥ ያመጣ ል።

መንግሥት ከ13 ፋብሪካዎች ውስጥ አሥር ፋብሪካዎች እንዲሸጡና የሚገኘው ገቢም የዕዳ ክፍያን ለማስተዳደር ወደ የሚቋቋመው ኮርፖሬሽን ሙሉ በሙሉ ፈሰስ እንዲደረግ በመወሰኑ፣ አሥሩ ፋብሪካዎች በተገመቱበት የሀብት መጠን ብቻ ቢሸጡ፣ ኮርፖሬሽኑ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ መቋቋሚያ ካፒታሉን ከስኳር ፋብሪካዎች ሽያጭ ያገኛል።

ከቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ገቢ ከፍተኛ ድርሻ ለኮርፖሬሽኑ ፈሰስ የሚደረግ ሲሆን፣ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘርፉን ለውጭ ገበያ ለመክፈት በተወሰነው መሠረት፣ ለሁለት የውጭ ኩባንያዎች የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ለመሰጥት የጨረታ ሒደት ተጠናቆ፣  አሸናፊዎቹ ኩባንያዎች ይፋ እንደሚደረጉ ይጠበቃል።

ጨረታ ያሸንፉት ሁለት ኩባንያዎች እያንዳንዳቸው ለ15 ዓመታት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ የሚያገኙ ሲሆን፣ የፈቃድ ክፍያ በትንሹ በአማካይ መንግሥት ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ሊያገኝ ይችላል፡፡

ለሁለት የውጭ ኩባንያዎች የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት በመካሄድ ላይ ካለው የጨረታ ሒደት ጎን ለጎን፣ መንግሥት በኢትዮ ቴሌኮም ላይ ያለውን 45 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮቴሌኮም ከፊል ሽያጭን አስመልክቶ እስካሁን ከተደረጉት ዝግጅቶች መካከል የተቋሙ አጠቃላይ ሀብትና ንብረት ግመታ፣ በውጭ የኦዲት ኩባንያ ተሠልቶ መጠናቀቁና ለመንግሥት መቅረቡ ይገኝበታል።

የኢትዮቴሌኮም ከፊል ሽያጭ እስኪጠናቀቅ የተካሄደው የሀብትና ንብረት ግመታ ውጤት በሚስጥር መጠበቅ አለበት፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሀብት በመንግሥት ከተገመተው 42 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጥቂት ወራት በፊት የኢትዮ ቴሌኮምን የተከፈለ ማቋቋሚያ ካፒታል ከ40 (አርባ) ቢሊዮን ብር ወደ 400 (አራት መቶ) ቢሊዮን ብር ማሳደጉ ይታወሳል።       (3)

 

{ሐ} የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ

በፍልውኃ አግልግሎት ድርጅች ሲተዳዳር የነበረው ላንጋኖ ሪዞርት 54 ሚሊዮን ብር ተሸጠ

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በፍልውኃ አገልግሎት ድርጅቶች ሥር ሲተዳደር የቆየውን የላንጋኖ ሪዞርት ሆቴል፣ ለቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ የሽርክና ማኅበር በ54 (ሃምሳ አራት) ሚሊዮን ብር ተሸጠ፡፡  የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሆቴሉን በተሻለ ሁኔታ በማልማት የአካባቢውን ወጣቶች የበለጠ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግእንዲችል በሽያጭ እንዲተላለፍለት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን ጠይቆ በተፈቀደለት መሠረት እንደሆነ ከኤጀንሲው ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ገዥው ቢፍቱ አዱኛ የሪዞርት ሆቴሉን ቋሚና ኮንትራት ሠራተኞች  በሙሉ ገዥው ተረክቦ፣ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅና የኅብረት ስምምነት፣ እንዲሁም የሙያ ደኅንነትና ሕግጋት ወይም መመርያዎች መሠረት እንደሚያስተዳድር በውሉ ላይ መጠቀሱ ተገልጿል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለ ሚካኤል በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዳሳሰቡ ተገልጿል፡፡ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የበቀለ ሞላ የላንጋኖና የሶደሬ የመዝናኛ ሆቴሎች በእጁ መዳፍ ውስጥ አድርጎል፡፡ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት ከኦሮሚያ እየተነቀለ በመውጣት ላይ ይገኛል፡፡    (4)

 

{መ} ወላቡ ኮንስትራክሽን Welabu Construction

ወላቡ ኮንስትራክሽን ከኦሮሚያ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የልማት ኮርፖሬሽን ጋር የአግሮ ኢንዱስትሪል ፓርክ በቡልቡላ (ምስራቅ ሸዋ ዞን)፣ የሻሸመኔ የገጠር መሸጋገሪያ ማዕከል (ምዕራብ አርሲ)፣ አጠቃላይ የግንባታ ወጪ 3.12 ሦስት ቢሊዮን መቶ ሃያ ሚሊዮን ብር  ለመስራት ውል ፈፅመዋል፡፡    (5)

“After establishment, WCSHC has signed six contracts with Oromia Industrial Park Development Corporation for the Construction of Integrated Agro-industrial Park at Bulbula (East Shoa Zone) and Rural Transformation Center at Shashemenne (West Arsi) with a total contract amount of ETB 3.12 Billion.”

 

{ሠ} የገቢዎችና የግብር ሚኒስቴር

የአዲስ አበባ ግብር ከፋዬችን ወደ ኦሮሚ ክልላዊ መንግሥት ግብር ከፋይነት በግድ በማዘዋወር

ወይዘሮ ታደለች አቤቤ የገቢዎች ሚኒስትር የአዲስ አበባ አንደኛ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ግብር ከፋዬችን ወደ ኦሮሚ ክልላዊ መንግሥት ግብር ከፋይነት በግድ በማዘዋወር የአዲስ አበባ ግብር ገቢ እንዲቀንስ የማድረግ የዘር ፖለቲካ ሴራ ላይ ተጠምዳ ከርማለች፡፡ የአዲስ አበባ የግብር ገቢ ከ40 እስከ 50 ቢሊዮን ብር ገቢ ከሚቀጥሉት ዓመታት ጀምሮ ገቢው በግማሽ ያህል ወደ ኦሮሚያ ክልል እንደሚዘዋወር በማድረግ የከተማዋ ገቢ እንደሚሽመደመድ የምጣኔ ኃብት ጠበብት አጋልጠዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ በቅንጅት በ1997እኢአ ምርጫ ቅንጅት እንዳሸነፈ ወያኔ የአዲስ አበባ ገቢ በመቀነስ፣ የአዲስ አበባን የፖሊስ ኃይል ምልመላ በማጠፍ፣ ፖሊስ ከሌላ ክልል እንዲመለመል በማድረግ ወዘተ የኢኮኖሚ አሻጥር ፈፅመው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ በአሁኑ ጊዜ ኦህዴድ/ ኦዴፓ የአዲስ አበባን ገቢ ወደ ኦሮሚያ ክልል የማዞር የኦሮሙማ የኢኮኖሚ የዘረፋ ሴራን ነው፡፡

ገቢዎች ሚኒስቴር 126 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

ገቢዎች ሚኒስቴር ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ባሉት አምስት ወራት 126.85 (መቶ ሃያ ስድስት) ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ባለፉት አምስት ወራት ከአገር ውስጥ ገቢ 80.96 (ሰማንያ) ቢሊዮን ብር፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 45.77 (አርባ አምስት) ቢሊዮን ብርና ከሎተሪ ሽያጭ 109.45 (መቶ ዘጠኝ) ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በበጀት ዓመቱ 290 (ሁለት መቶ ዘጠና) ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱንና በመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ከ126 (መቶ ሃያ ስድስት) ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታውቆል፡፡ ገቢው ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ17.4 ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል፡፡ በታኅሳስ ወር 21.33 (ሃያ አንድ) ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶል፡፡ በተመሳሳይ ወራት ውስጥ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ ባደረጉት እንቅስቃሴ፣ 1,356,000,119 (አንድ ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውም ተገልጿል፡፡ ግምታዊ ዋጋቸው 981,590,000 ብር ለመያዝ ታቅዶ 1,100,631,000 ብር የሚገመት ገቢ ኮንትሮባንድን ለመያዝ መቻሉን፣ የገቢ ኮንትሮባንድ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ24 በመቶ ጭማሪ ሲያሳይ ወጪ ኮንትሮባንድ ደግሞ 72 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል፡፡       (6)

 

 

ምንጭ፡-

 

Leave a Reply