በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሩሲያ ምክትል ተጠሪ ዲሚትሪ ፓሊያኒስክ ወቅታዊ በሆኑ አለምአቀፍ ጉዳዮች መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ፓሊያኒስክ ሲናገሩ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ሩሲያ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን ገልፀው፤ የውጭ ሃይሎች ከጣልቃ ገብነት እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል።

አምባሳደሩ በመግለጫቸው ” ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ግጭት የአለምአቀፍ ሃይላት ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዳለ ከኢትዮጵያውያን ወዳጆቻችን እንሰማለን። ሊታወቅ የሚገባው ይህ አደገኛ መሆኑን ነው ። ” ብለዋል።

ምክትል ተጠሪ ፓሊያንስኪ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሩሲያ አቋም የፀና መሆኑንም እንዲህ ሲሉ አስምረውበታል።

” እኛ ከጅምሩ በኢትዮጵያ ውጣዊ ግጭት ምዕራባውያን ጣልቃ እንዳይገቡ አስጠንቅቀናል ፤ በድብቅም ቢሆን መሞከር እንደሌለባቸው ጭምር አስጠንቅቀናል “

ሩሲያ በተለያዩ አለምአቀፍ መድረኮች ግጭቱ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ባከበረ መልኩ እንዲፈታ እንደምትፈለግ ስትገልፅ ቆይታለች።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply