በመንግስትና ህወሓት መካከል የሚደረገው ድርድር ሁሉንም ያሳተፈ ኢንዲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም…

በመንግስትና ህወሓት መካከል የሚደረገው ድርድር ሁሉንም ያሳተፈ ኢንዲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የሀገራዊ ምክክሩን ሂደት የሚከታተል ቡድን ማቋቋሙን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የኢፌዴሪ መንግስት እና ህወሓት ድርድር ሂደት ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነ ገልጧል። የሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታን በተመለከተ ምክር ቤቱ ሚናን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሄኖክ መለሰ፤ ምክር ቤቱ የሀገሪቱ ሁኔታ በቅርበት እንደሚከታተልና ይበጃሉ ያላቸውን ሃሳቦች እንደሚያቀርብ ተናግረዋል። ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን የሰላም ድርድር ሂደቱ ሁሉንም ቁልፍ ባለድርሻ አካላት በተለይም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ያሳተፈ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህም የሰላም ድርድር ሂደቱ ቅቡልነት እንዲኖረው ከማድረግ ባለፈ ውጤቱ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ እንዲችል ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል ብለዋል። ምክር ቤቱ፤ እንደ “ሀገራዊ ምክክር” በመሳሰሉ ቁልፍ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የራሱን አስተዋጽዖ ለማበርከት እንቅስቃሴ እንደጀመረም አስታውቀዋል። “ምክር ቤቱ ከሲቪል ማህበረሰቡ የተውጣጣና ሀገራዊ የምክክር ሂደቱን የሚከታተል ወይም የ’ሪፈረንስ’ ቡድን አቋቁሟል” ብለዋል። አሁን በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ዘርፈ ብዙና የተወሳሰቡ ችግሮችን የመፍታት ጉዳይ ለመንግስት ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነትና ተግባር የሚጠይቅ መሆኑም አስገንዝበዋል። በተለያዩ ምክንያቶች የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ለማለት እንደማይደፍሩ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ለአስር አመታት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች “በሰላም ጉዳይና በዴሞክራሲ ግንባታ” በመሳሰሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው በህግም ጭምር ገደብ ተጥሎ መቆየቱ በምክንያትነት አንስተዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከተመሰረተ አንድ ዓመት ከስድስት ወር እንደሆነውና ከስሩ አራት ሺህ የሚደርሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የያዘ መሆኑ ተገልጧል። ለዘገባው አል ዐይንን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply