You are currently viewing በመንግስት መዋቅር ሳይታቀፉ በራሳቸው ተነሳሽነት በጫካ ሆነው የአሸባሪውን ትሕነግ ጦር እየተፋለሙ ለሚገኙ ለራያ ሚሊሻዎች እና ለፋኖዎች ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 1…

በመንግስት መዋቅር ሳይታቀፉ በራሳቸው ተነሳሽነት በጫካ ሆነው የአሸባሪውን ትሕነግ ጦር እየተፋለሙ ለሚገኙ ለራያ ሚሊሻዎች እና ለፋኖዎች ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1…

በመንግስት መዋቅር ሳይታቀፉ በራሳቸው ተነሳሽነት በጫካ ሆነው የአሸባሪውን ትሕነግ ጦር እየተፋለሙ ለሚገኙ ለራያ ሚሊሻዎች እና ለፋኖዎች ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመንግስት መዋቅር ሳይታቀፉ በራሳቸው ተነሳሽነት በጫካ ሆነው የአሸባሪውን ትሕነግ ጦር በቆረጣ፣ በደፈጣና መንገድ በመዝጋት እየተፋለሙ ለሚገኙ የራያ ሚሊሻዎች እና ለፋኖዎች ድጋፍ ማድረጉን ወሎ ቤተ አምሐራ የበጎ አድራጎት ድርጅት አስታውቋል። የግብርና ስራቸውን ትተው ለህልውና ትግሉ በመዝመትና “ለአሸባሪው ትሕነግ እጅ አንሰጥም” በማለት በጫካ ሆነው እየተፋለሙ ለሚገኙ በወሎ ለራያ ሚሊሻዎች ነው የ90 ኩንታል የምግብ ዱቄት ድጋፍ የተደረገው። አሚማ ከማህበሩ መስራችና አመራር ከሆኑት መካከል ከይርጋለም ታደሰ ጋር ከነበረው ቆይታ እንደተረዳው አሁን ቀደም በርካታ በጎ ተግባራትን በማከናወን የሚታወቀው የወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት በቅርቡ ህጋዊ እውቅና አግኝቷል። የወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጂቶች ባለስልጣን በአገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት /NGO/ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ከ ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በምዝገባ ቁጥር 5902 በባለስልጣኑ ተመዝግቦ ህጋዊ የመንግስት ፈቃድ አግኝቷል። በመንግስት በኩል የተሰጠው ህጋዊ እውቅና በመላው ኢትዮጵያ ተንቀሳቅሶ ለመስራት እንደሚያስችለው ተገልጧል። ይህ ከተመሰረተ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ድርጅት ነው ወደ ወሎ ራያ በማቅናት በቆቦ ዞብል ግንባር ተገኝቶ የአቅርቦት ችግር አጋጥሟቸው ለነበሩ በመንግስት መዋቅር ሳይታቀፉ የሽብር ቡድኑን እየተፋለሙ ላሉ የአርሶ አደር ሚሊሻዎች እና ፋኖዎች የ90 ኩንታል የምግብ ዱቄት ያበረከተው። ድርጅቱ ከደብረብርሃን ዱቄት ፋብሪካ ጥራቱን የጠበቀ የምግብ የስንዴ ዱቄት በቅናሽ ዋጋ እንዲገኝ እና አጠቃላይ ከደብረብርሃን በመነሳት በአፋር በኩል በማቋረጥ ራያ ዞብል እንዲደርስ በማስተባበር ትልቅ እገዛ ላደረጉ በሚል አቶ ደሳለኝ አንዳርጌን አመስግኗል። በተጨማሪም የተጣለባቸውን አደራ አስቸጋሪ የሆነውን ውጣ ውረድ የበዛበት ጉዞን በማለፍ ሀላፊነታቸውን ለተወጡ ሮዛ ሰለሞን ፣ አስካል ታደሰ እና ሻምበል እንዲሁም በቦታው በጥሩ ሁኔታ እንዲከፋፈል በተግባር የተባበሩን በሚል አድማሱ ይመር፣ሞገስ አማረ ፣ አድኖ አቸነፍ ፣ፋኖ አድማሱ ፈንታው እና የራያ ሚሊሻዎችን በሙሉ አመስግኗል። የወሎ ፋኖ መሪ የሆኑት ፋኖ ምህረት ወዳጆ (ምሬ) በወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት በኩል የተደረገው የ90 ኩንታል የምግብ ድቄት የደረሳቸው መሆኑን በመግለጽ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply