በመንግስት እና በህወሓት መካከል እየተካሄደ ባለው ንግግር ላይ “ከፍተኛ የውጭ ጣልቃገብነት” እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ

ማክሰኞ ጥቅምት 22 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ያለውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት እየተካሄደ ባለው የሰላም ንግግር ላይ “ከፍተኛ የውጭ ጣልቃገብነት” እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሲጂቲኤን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሰላም ንግግሩ ላይ “ከፍተኛ የውጭ ጣልቃገብነት” እንዳለ ገልጸው፤ “ህወሓት ህገመንግስቱን እንዲያከብር እና ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አንድ ክልል” እንዲንቀሳቀስ ለማሳመን ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም ህወሓት “ፍላጎችንን መገንዘብ የሚችሉ ከሆነ እና የራሱን ህገመንግስት የሚያክብር እና በህጉ መሰረት የሚንቀሳቀስ ከሆነ ሰላም ይሰፍናል ብየ አስባሁ” ብለዋል።

በኢትዮጵያ ጉዳይ “በግራ በቀኝ ብዙ ጣልቃገብነት” መኖሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ኢትዮጵያውያን መረዳት ያለባቸው የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን መፍታት እንደምንችል ነው።” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በአፍሪካ ህብረት መሪነት በፌደራሉ መንግስት እና በህወሓት መካከል ባለፈው ሳምንት ሰኞ በደቡብ አፍሪካ የተጀመረው ድርድር የቀጠለ ሲሆን፤ በመጪው እሁድ እንደሚጠናቀቅ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል።

The post በመንግስት እና በህወሓት መካከል እየተካሄደ ባለው ንግግር ላይ “ከፍተኛ የውጭ ጣልቃገብነት” እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply