በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የነበሩ የጁንታው ተባባሪዎች ሦስት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ሁሉንም መፈጸማቸውን ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ….

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የነበሩ የጁንታው ተባባሪዎች ሦስት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ሁሉንም መፈጸማቸውን ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የነበሩ የጁንታው ተባባሪዎች ከባንዳው የህወሓት ቡድን ሦስት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ሁሉንም መፈጸማቸውን ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ አስታውቀዋል። ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት፤ የጁንታው ተባባሪ የሆኑ የሰራዊቱ አባላት፣ የክልሉ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻዎችና ኦነግ ሸኔ ከከሀዲው የህወሓት ቡድን የተሰጣቸውን የባንዳ ተልዕኮ ተቀብለው ፈፅመዋል፤ ሰራዊቱን ወግተዋል። እንደ ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ገለጻ፤ ተልዕኮዎቹም ሠራዊቱን ከውስጥ ማፍረስ፣ ሠራዊቱን መውጋት፣ እና ማዘናጊያ የሽምግልና ስራ መስራት የሚሉ ነበሩ፤ ባንዳዎቹ ሁሉንም ፈፅመውታል። ሠራዊቱን ከውስጥ ለማፍረስ የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ አዲስ አበባ በሚገኘው የመገናኛ ሀላፊ አማካኝነት ወደነሱ አዙረዋል ያሉት ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ፤ በዚህም ከመከላከያ ጋር እና ጦሩም እርስ በርሱ እንዳይገናኝ አድርገዋል፤ የሠራዊቱን የወር ደሞዝ እና ቀለቡን ወስደዋል፤ አዛዦችንም አፍነዋል ነው ያሉት። “ሠራዊታችን ይህ ሁሉ ተፈፅሞበት ተዋግቷቸዋል፤ ጀግንነትም ፈፅሟ” ያሉት ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ፤ ውጊያው ከክልሉ ልዩ ሀይል ጋር ብቻ እንዳልነበረ አብራርተዋል። በዛላንበሳ፣ በሽራሮ ፣ በራማ ፣ በፆረና እና በሌሎች ቦታዎች የኦነግ ሸኔ አባላት ባንዲራቸውን ይዘው አብረው ሰራዊቱን እንደወጉ ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ አስታውቀዋል። ቢቢሲ አማርኛ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply