“በመካከላችን የነበሩ የከሀዲው ህወሓት ተላላኪ አመራሮች ለሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ያቀረቡልን አማራጭ ከእኛ ጋር ሁኑ አሊያም በህይወታችሁ ወስኑ የሚል ነበር”  – ከስፍራው ያመለጠ የሰራዊ…

“በመካከላችን የነበሩ የከሀዲው ህወሓት ተላላኪ አመራሮች ለሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ያቀረቡልን አማራጭ ከእኛ ጋር ሁኑ አሊያም በህይወታችሁ ወስኑ የሚል ነበር” – ከስፍራው ያመለጠ የሰራዊ…

“በመካከላችን የነበሩ የከሀዲው ህወሓት ተላላኪ አመራሮች ለሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ያቀረቡልን አማራጭ ከእኛ ጋር ሁኑ አሊያም በህይወታችሁ ወስኑ የሚል ነበር” – ከስፍራው ያመለጠ የሰራዊቱ አባል አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ “በመካከላችን የነበሩ የከሀዲው ህወሓት ተላላኪ አመራሮች ለሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ያቀረቡልን አማራጭ ከእኛ ጋር ሁኑ አሊያም በህይወታችሁ ወስኑ የሚል ነበር” ሲል ከስፍራው ያመለጠ የሰራዊቱ አባል ተናገረ። የሰሜን ዕዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር አባል የሆነው ሻለቃ አምሳሉ ደመቀ ከመከላከያ ቴሌቪዥን ጋር በነበረው ቆይታ ላይ እንደተናገረው፤ ከሀዲው የህወሓት ቡድን ታጣቂዎች በሰራዊቱ ውስጥ ካሉ የእነሱ አይነት ተባባሪ ከሀዲዎች ጋር በመሆን በክፍለ ጦሩ ላይ ሌሊት ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ለሰራዊቱ ያቀረቡት አማራጭ ከእኛ ጋር ወግኑ አሊያም በህይወታችሁ ወስኑ የሚል ነበር። የክፍለ ጦሩ ሰራዊት አባላት አገር ወዳድ በመሆናቸው የቀረበውን ከእኛ ጋር ወግኑ አማራጭ እንዳልተቀበሉት የተናገረው ሻለቃ አምሳሉ፤ ከሃዲው የህወሓት ቡድን መሳሪያ የሚቀመጥበትን ቦታ ተቆጣጥረው ከዘረፉና ጭነው ከወሰዱ በኋላ መግደል የፈለጉትን ገድለዋል፤ የተረፈውን ሰራዊት ልብሱን አስወልቀው ርቃኑን በማድረግ ወደ አዳራሽ አስገብተው እንዳፈኗቸው አብራርቷል። የሰራዊቱ አባላት በክልሉ ከ20 አመት በላይ የኖሩ በመሆናቸው ተጋብተዋል፤ ልጆችች ወልደዋል ያለው ሻለቃው፤ በእለቱ የተፈጠረውን ዘግናኝ ድርጊት በመስማት ከሰራዊቱ አባላት ጋር የተጋቡ እናቶችና ህጻናት ወደ ካምፕ በመምጣት ቤተሰቦቻቸው ላይ የተደረገውን ድርጊት ተመልክተው ሲያሰሙት የነበረው ዋይታና ድርጊት ሁሉንም የሚረብሽ እንደነበረ አብራርቷል። ከሀዲው የህወሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓም ሌሊት ጥቃት በመፈጸም ብዙዎች ዘግናኝ በሆነ መልኩ እንደገደለና የተቀሩትን አፍኖ እንደወሰደ ይታወሳል። ይሄንን ተከትሎ እየተወሰደ ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ ጁንታው ከፍተኛ ኪሰራ እየደረሰበት በመሆኑ እንደ ማይካድራ ባሉ ከተሞች በንጹሀን ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙ ይታወሳል። በዚህም አሜሪካን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዳወገዙት ይታወቃል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Source: Link to the Post

Leave a Reply