በመዲናዋ በአዲስ ዓመት ዋዜማና በበአሉ ዕለት በትራፊክ ግጭት የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ::በዋዜማው ዕለት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ብስራት ትምህርት ቤት አ…

በመዲናዋ በአዲስ ዓመት ዋዜማና በበአሉ ዕለት በትራፊክ ግጭት የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ::

በዋዜማው ዕለት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ብስራት ትምህርት ቤት አካባቢ በተከሰተ የትራፊክ ግጭት በግምት የ35 ዓመት ወጣት ህይወቱን ሊያጣ ችሏል፡፡

እንዲሁም ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ባጋጠመ የትራፊክ ግጭት በግምት የ60 ዓመት እናት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በበዓሉ እለት ከቀኑ 11፡00 አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ወረዳ 7 አካባቢ በተከሰተ የባቡር አደጋም የአንድ የ30 ዓመት ወጣት ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በበአሉ ዋዜማ እና በበአሉ ቀን ምንም አይነት የእሳት አደጋ እንዳልተከሰተ ነው የተገለጸው፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ጀሞ አካባቢ ከደረሰው አነስተኛ የጎርፍ አደጋ ውጪ ምንም ድንገተኛ አደጋ አለመድረሱን ተናግረዋል፡፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል

መስከረም 03 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply